ትናንት ማምሻውን ላይ በተከናወነው የቲክቶክ የይዘት ፈጠራ ውድድር አዘጋጆች እና አጋር አካላት ላይ ቅሬታ ቀረበ።

Reading Time: 2 minutes
የቅን ልቦች በጎ ሥራ ድርጅት ከ2013ዓ.ም ጀምሮ ማህበራዊ ሚዲያን ለሀገርና ሰላም ግንባታ እናውል ፤ልዩነታችንን ሳይሆን አንድ የሚያደርጉንን እናጎልብት በማለት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ስልጠናዎችን እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን በዚህ አመት በሙሁራን በተዘጋጀ መመዘኛ በ20 ዘርፍ 100 ምርጥ ተፅእኖ ፈጣሪ የማህበራዊ ሚዲያ ባለሙያ ለህዝብ ለማሳወቅ በዝግጅት ላይ በሚገኝበት ወቅት በቅን ልቦች በጎ ሥራ ድርጅት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞችን ሌሎች አካላት በማስኮብለን ላለፉት ሶስት አመታት የተደከመበትን የሀሳብ በመወሰድ ትናንት ምሽት የቲክቶክ የይዘት ፈጠራ ውድድር በማለት አዘጋጅተዋል።

ቅን ልቦች በጎ ሥራ ድርጅት ይኸ ከመከወኑ አስቀድሞ ለኘሮግራሙ አዘጋጆች እና ለኘሮግራሙ አጋር አካላቶች ያሳወቀ ሲሆን ሁለቱም አጋር አካላት (ቢጂአይ ኢትዮጵያ እና ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ) ቅን ልቦች ከአዘጋጁ ዩኒየን ኢቨንት ጋር ተቀራርበው እንደአስማማቸው የቅን ልቦች በጎ ሥራ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ስንሻውለየኔ ቫይብ ዝግጅት ክፍል በስልክ የገለጹልን
ሲሆን ትናንት ማምሻውን በተከናወነው የእውቅና እና ሽልማት መርሐግብር አስቀድሞ ከተደረሰባቸው ስምምነቶች ውጪ በመከናወኑ የቅን ልቦች በጎ ሥራ ድርጅት በኘሮግራሙ አዘጋጅ በሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና በቢጂአይ ኢትዮጵያ ላይ ቅሬታውን አቅርቧል።

ጉዳዩን አስመልክቶ የኔ ቫይብ ዝግጅት ክፍል
የዩኒየን ኢቨንትስ ስራ አስኪያጅ አቶ ሰሎሞን የእጅ ስልክ ላይ ደጋግመን ብንደውልም የእጅ ስልካቸው ዝግ በመሆኑ በዚህ ዘገባ ያላካተትን ሲሆን በቀጣይ አቶ ሰሎሞን የሚሉት ነገር ካለ የየኔ ቫይብ ዝግጅት ክፍል ለማስተናገድ ዝግጁ ነው።

ዩኒየን ኢቨንት ባሰናዳው በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነው የቲክቶክ የይዘት ፈጠራ ውድድር ላይ
በተለያዩ ምድቦች ውስጥ 1280 የሚሆኑ ቲክቶከሮች በዊብሳይት አማካኝነት ታጨተው እና ከእነሱም መካከል100 የቲክ ቶክ ተፅእኖ ፈጣሪዎች ተመርጠው በልዮ ልዩ ዘርፍ በህዝብ እና በዳኞች የተመረጡ ቲክቶከሮች የዋንጫ እና ከ50 ሺህ እስከ አራት መቶ ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

62190cookie-checkትናንት ማምሻውን ላይ በተከናወነው የቲክቶክ የይዘት ፈጠራ ውድድር አዘጋጆች እና አጋር አካላት ላይ ቅሬታ ቀረበ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE