በአርትስ ቴሌቪዥን የሚቀርበው በህግ አምላክ የቴሌቪዥን ድራማ ምእራፍ ሁለት የፊታችን እሁድ ሕዳር 2 ቀን 2016 ዓ.ም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ለተመልካቾች መቅረብ እንደሚጀምር የአርትስ ቴሌቪዥን ረዳት ቺፍ ኦፕሬሽናል ኦፊሰር አቶ ራፍቶኤል ወርቁ ዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2016 የድራማውን መጀመር አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
አርትስ ቴሌቪዥን ኤክስክቲዩቭ ፕሮዲውሰር ያደረገው «በሕግ አምላክ» ድራማ በደራሲ እና ሕግ ባለሙያው ሙልጌታ አረጋዊ የተጻፈው ሲሆን በአበበ ባልቻ ፕሮዲዩስ ተደርጎ በሰው ለሰው እና በዘመን ድራማ በምናውቀው አርቲስት ሰለሞን አለሙ የተዘጋጀ ልብ አንጠልጣይ ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ነው።
«በሕግ አምላክ » ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ደረጃውን በጠበቀ ፕሮዳክሽን የተሰራ እና ከፍተኛ ገንዘብ ወጪ የተደረገበት ሲሆን አርትስት ቴሌቪዥን ኪነ ጥበብን ለማብረታታ የሚያደርገውን ተግባር አጠናቅሮ እንደሚቀጥል በመግለጫው ተገልጿል ።
ባለፉት አምስት አመታት ውስጥ አርትስ ቴሌቪዥን የተለያዩ አዝናኝ እና ቁምነገር አዘል የሆኑ የመዝናኛ ኘሮግራሞችን በማዘጋጀት በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የመዝናኛ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች መካከል በግንባር ቀደምነት የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ በአዳዲስ ይዘት ያላቸውን እና ነባር ኘሮግራሞች ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝ አቶ ራፍቶኤል ወርቁ ገልጸዋል።
614700cookie-check«በሕግ አምላክ» ድራማ የፊታችን እሁድ ሕዳር 2 ቀን 2016 ዓ.ም ይጀምራል።no