የወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማኅበር መስከረም 1 ቀን 1990 ዓ.ም ከህይወት ገጠመኛቸው በተማሩት በአቶ ስንታየሁ አበጀ ተነሳሽነት የተመሰረቶ በአሁኑ ሰዓት በማዕከሉ ከ200 በላይ ሰዎችን ህክምና፣ የተመጣጠነ ምግብ እና ንፅህናቸው በተጠበቀ መልኩ እያኖረ ሲሆን በተጨማሪ 100 ሰዎችን በተመላላሽነት እየመገበና እያለበሰ ያለ አንጋፋ ማኅበር ነው።
ይህ ማህበር ላለፉት 25 ዓመታት ለሀገር እጅግ ከፍተኛ ውለታ የዋሉና በማምሻ ዕድሜያቸው ግን ጧሪና ቀባሪ አጥተው በየጎዳናውና በተለያዩ የቤተ ዕምነቶች አጥር ሥር ወድቀው የሚገኙ አረጋውያንንና አቅመ ደካማ ወገኖችን ዘር ፆታ ሃይማኖት ሳይለይ ከወደቁበት እያነሳ እየጦረ ፣ እያሳከመ ፣ እየተንከባከበ በማዕከል ደረጃ በቀደምትነት ሲሰራ ቆይቷል።
ይህ ተቋም ምንም ዓይነት ቋሚ የገቢ ምንጭ ሳይኖረው ከመንግሥት ጎን በመቆም የበኩሉን እገዛ በማድረግ ይህንን ትልቅ የአገር ራዕይ የሆነና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖችን በማስተባበር የሠራው ሥራ እኛ ኢትዮጵያውያን የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላችን እጅግ የሚያኮራን መሆኑን በሚያሳይና ለትውልድ በሚያስተምር መልኩ የተመሠረተበትን 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል በማስመልከት በተከታታይ ስለሚያከብራቸው መርሀ ግብሮች ዛሬ ጥቅምት 22 ቀን 2016 በብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ ውስጥ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መግለጫ የሰጠ ሲሆን አያይዞም የፎቶ አውደ ርዕይ ላይ የክብር እንግዳው የሴቶች ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር የሚኒስተር አማካሪ አቶ ሰለሞን አስፋው እና የኢትዮጵያ አርበኞች ህብረት ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቲ በተገኙበት የፎቶ ዐውደ ርዕይ መርሀ ግብር በይፋ ተከፍቷል።
እስከ ህዳር 2 ቀን 2016 ዓ.ም በሚቆየው በፎቶ ግራፍ አውደ ርዕዩ ላይ የማህበሩ መስራች አቶ ስንታየሁ አበጀ
ሁሉም ሰው በነጻ መጥቶ እንዲጎበኝ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ከታች በተቀመጠው የባንክ አካውንት ሁሉም የአቅሙን ቢረዳ አረጋውያንና ህሙማንን እንደ መርዳት ይቆጠራልም ብለዋል።
ንግድ ባንክ 1000409721374
አዋሽ ባንክ 01304210305400
ህብረት ባንክ 1141116102721018
ዳሽን ባንክ 0253247601011
ቡና ባንክ 3849601000003/(384/3/CA)
Coop ኦሮሚያ ባንክ 1013700020957
አቢሲኒያ ባንክ 64327728
ንብ ባንክ 7000024533579/(118CUR50)
አባይ ባንክ 1522117408080017
614300cookie-checkየወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማኅበር የ25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዮ በዓል እያከበረ ነው!no
ይህ ማህበር ላለፉት 25 ዓመታት ለሀገር እጅግ ከፍተኛ ውለታ የዋሉና በማምሻ ዕድሜያቸው ግን ጧሪና ቀባሪ አጥተው በየጎዳናውና በተለያዩ የቤተ ዕምነቶች አጥር ሥር ወድቀው የሚገኙ አረጋውያንንና አቅመ ደካማ ወገኖችን ዘር ፆታ ሃይማኖት ሳይለይ ከወደቁበት እያነሳ እየጦረ ፣ እያሳከመ ፣ እየተንከባከበ በማዕከል ደረጃ በቀደምትነት ሲሰራ ቆይቷል።
ይህ ተቋም ምንም ዓይነት ቋሚ የገቢ ምንጭ ሳይኖረው ከመንግሥት ጎን በመቆም የበኩሉን እገዛ በማድረግ ይህንን ትልቅ የአገር ራዕይ የሆነና በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖችን በማስተባበር የሠራው ሥራ እኛ ኢትዮጵያውያን የመረዳዳትና የመደጋገፍ ባህላችን እጅግ የሚያኮራን መሆኑን በሚያሳይና ለትውልድ በሚያስተምር መልኩ የተመሠረተበትን 25ኛ ዓመት የብር ኢዮቤልዩ በዓል በማስመልከት በተከታታይ ስለሚያከብራቸው መርሀ ግብሮች ዛሬ ጥቅምት 22 ቀን 2016 በብሔራዊ ሙዚየም አዳራሽ ውስጥ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መግለጫ የሰጠ ሲሆን አያይዞም የፎቶ አውደ ርዕይ ላይ የክብር እንግዳው የሴቶች ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር የሚኒስተር አማካሪ አቶ ሰለሞን አስፋው እና የኢትዮጵያ አርበኞች ህብረት ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቲ በተገኙበት የፎቶ ዐውደ ርዕይ መርሀ ግብር በይፋ ተከፍቷል።
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ
ሁሉም ሰው በነጻ መጥቶ እንዲጎበኝ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ከታች በተቀመጠው የባንክ አካውንት ሁሉም የአቅሙን ቢረዳ አረጋውያንና ህሙማንን እንደ መርዳት ይቆጠራልም ብለዋል።
ንግድ ባንክ 1000409721374
አዋሽ ባንክ 01304210305400
ህብረት ባንክ 1141116102721018
ዳሽን ባንክ 0253247601011
ቡና ባንክ 3849601000003/(384/3/CA)
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን
አቢሲኒያ ባንክ 64327728
ንብ ባንክ 7000024533579/(118CUR50)
አባይ ባንክ 1522117408080017