ላየን ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሆቴልና ቢዝነስ ኮሌጅ 557 ተማሪዎችን አስመረቀ።

Reading Time: 2 minutes
ላየን ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሆቴልና ቢዝነስ ኮሌጅ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብር በሆቴል ማኔጅመንት ፣በማርኬቲንግ ማኔጅመንትና በአካውንቲንግና ፋይናንስ በቴክኒክና ሙያ መርሃ ግብር በደረጃ 4 በምግብ እና መጠጥ አገልግሎት ቁጥጥር ፣ ቱር ጋይድ ሰርቪስ ፣በአካውንቲንግና ፋይናንስ ፣ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት ፣ ፍሮንት ኦፊስ ሱፐርቪዥን ፣ ቱር ኦፕሬሽን እና በምግብ አቅርቦት በመገናኛና በአራትኪሎ 70 ደረጃ ካምፓሶቹ ያስተማራቸውን 557 ተማሪዎች ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2016 ዓ.ም በአምባሳደር የሲኒማ አዳራሽ አስመርቋል።

ኮሌጁ ከተመሰረተበት ከ1995ዓ. ም ጀምሮ በተለይም በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ያለውን የተማረ የሰው ኃይል ለመቅረፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን የመክፈል አቅም ለሌላቸው እንዲሁም የሙያው ፍላጎት ላላቸውና ሞያቸውን በሳይንስ በተደገፈ ትምህርት ማሳደግ ለሚፈልጉ እንደ ጥሩ አማራጭ ሆኖ በማገልገል ላይ ይገኛል።

የኮሌጁ መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ መሀመድ አወል ተመራቂዎች በተማሩት ዘርፍ ሀገራቸውንና ህብረተሰቡን በቅንነት እንዲያገለግሉ፣ ስራ ፈላጊ ሳይሆኑ ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ አደራ በማለት የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈው ላየን ኢትዮጵያ በሆቴል ቱሪዝምና ቢዝነስ ዘርፎች ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን ይቀጥላል ብለዋል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ ዶክተር ፍጹም አባተ በአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ የቴክኒክ አማካሪ ለተመራቂዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ ተመራቂዎች በቀሰሙት ዕውቀትና ክህሎት የሞያው ስነ ምግባር በሚፈቅደው መሰረት ተግባራዊ እንዲያደርጉ የአደራ ቃል አስተላልፈው በሆቴል ቢዝነስ ኢንዱስትሪው በሚፈቅደው ልክ ተግባራዊ እንደምታደርጉ እምነት አለኝ ያሉ ሲሆን በዘርፉ የሚሰለጥኑ ተማሪዎችን ከሀገር ውስጥ አልፎ በተለያዩ ሀገራት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማብቃት እንደ ሀገር ያስፈልጋል ብለዋል።

ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በ20 ዓመታት ውስጥ የዛሬዎቹን ተመራቂዎች ሳይጨምር በድምሩ ከአስራ አንድ ሺ በላይ ባለሙያዎችን በማሰልጠን ለዘርፉ ያበረከተ ሲሆን ከዛሬዎቹ ተመራቂዎች መካከልም ረዳት የሌላቸውንና ከፍለው መማር ላልቻሉ ነጻ የትምህርት እድል በመስጠት ስልጠናቸውን እንዲያጠናቅቁ በማድረግ ተቋማዊ ማኀበራዊ ሃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል፡፡

60790cookie-checkላየን ኢትዮጵያ የቱሪዝም ሆቴልና ቢዝነስ ኮሌጅ 557 ተማሪዎችን አስመረቀ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE