የአልበሙን የምርቃት ሥነ- ሥርዓት አስመልክቶ ዛሬ ጥቅምት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ማምሻውን በሸራተን አዲስ ሆቴል በተሰጠው መግለጫ የአልበሙ ምርቃት የፊታችን ቅዳሜ ጥሪ የተደረገላቸው የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም የአርቲስቱ አድናቂዎች በተገኙበት እንደሚከናወን ተገልጿል።
የበርካታ ግጥምና ዜማ ደራሲ የሆነው ተወዳጁ ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አበበ የሙዚቃ አልበም ከብላክ ፐርል ባርና ላውንችና ከኤላ ቴቪ ጋር በመተባበር በቅርቡ ለአድማጮች መቅረብ የሚታወስ ሲሆን ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ የሚሰራቸውን የሙዚቃ ኮንሰርቶች፣ የማስታወቂያ ሥራዎችን እንዲሁም የበጎ አድራጎት ሥራዎች ከብላክ ፐርል ጋር በጋራ እንደሚሰራ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።
አልበሙ በሀገራችን ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስራዎቻቸውን ለአድማጭ በማድረስ በአጭር በግጥም በዜማ እንዲሁም በትንበር አሻራቸውን ያሳረፉበት በርካታ ዝግጅት ሲደረግበት የነበረ አልበም ከመሆነም በላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነትና ተወዳጅነትን አትርፏል።
«ማለፊያ» በውስጡ አሥራ ሁለት የሙዚቃ ሥራዎች የተካተቱበት ሲሆን፤ በርካታ ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሞያዎች አሻራቸውን አሳርፈውበታል።
አርቲስቱ ከዚህም ሌላ ለበርካታ አንጋፋ እና ወጣት አርቲስቶች የግጥምና የዜማ ስራዎችን በመስራት እና በመስጠት የሚታወቅ ሲሆን ለመጥቀስም ያህል ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ፣ ሄለን በርሄ፣ ቬሮኒካ አዳነ፣ ሐይማኖት ግርማ ሃሌሉያ ተክለፃዲቅ ድምፃዊ ያሬድ ነጉ እና ለእነዚህና ለሌሎች ለበርካታ አርቲስቶች ስራዎችን በመስጠት ይታወቃል።
605700cookie-checkየድምፃዊ ብስራት ሱራፌል« ማለፊያ » የተሰኘው አዲስ አልበም የፊታችን ቅዳሜ ይመረቃል።no
የበርካታ ግጥምና ዜማ ደራሲ የሆነው ተወዳጁ ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አበበ የሙዚቃ አልበም ከብላክ ፐርል ባርና ላውንችና ከኤላ ቴቪ ጋር በመተባበር በቅርቡ ለአድማጮች መቅረብ የሚታወስ ሲሆን ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ የሚሰራቸውን የሙዚቃ ኮንሰርቶች፣ የማስታወቂያ ሥራዎችን እንዲሁም የበጎ አድራጎት ሥራዎች ከብላክ ፐርል ጋር በጋራ እንደሚሰራ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።
አልበሙ በሀገራችን ሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ ስራዎቻቸውን ለአድማጭ በማድረስ በአጭር በግጥም በዜማ እንዲሁም በትንበር አሻራቸውን ያሳረፉበት በርካታ ዝግጅት ሲደረግበት የነበረ አልበም ከመሆነም በላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተቀባይነትና ተወዳጅነትን አትርፏል።
«ማለፊያ» በውስጡ አሥራ ሁለት የሙዚቃ ሥራዎች የተካተቱበት ሲሆን፤ በርካታ ወጣት እና አንጋፋ የሙዚቃ ባለሞያዎች አሻራቸውን አሳርፈውበታል።
አርቲስቱ ከዚህም ሌላ ለበርካታ አንጋፋ እና ወጣት አርቲስቶች የግጥምና የዜማ ስራዎችን በመስራት እና በመስጠት የሚታወቅ ሲሆን ለመጥቀስም ያህል ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ፣ ሄለን በርሄ፣ ቬሮኒካ አዳነ፣ ሐይማኖት ግርማ ሃሌሉያ ተክለፃዲቅ ድምፃዊ ያሬድ ነጉ እና ለእነዚህና ለሌሎች ለበርካታ አርቲስቶች ስራዎችን በመስጠት ይታወቃል።
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን