መልካም የበጎ አድራጎት ተግባር

Reading Time: 2 minutes
የባህርዳር ከነማ ተጫዋቾች እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች
በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ለሚገኙ ከ700 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የምሳ ግብዣ አደረጉ።

የዘመን መለወጫ በዓልን በማስመልከት በማዕከሉ አምባሳደር በሆነው በወጣት ሰሎሞን ገብረማርያም አስተባባሪነት የባህርዳር ከነማ ተጫዋቾች እና የኪነጥበብ ባለሙያዎች በተገኙበት ባሳለፍነው መስከረም 1 ቀን 2016 ዓ.ም ቁስቋም አካባቢ በሚገኘው በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል ለሚገኙ ከ700 በላይ ዜጎች የምሳ ግብዣ አደረገ።

ወጣት ሰሎሞን ገብረማርያም በመርሐግብሩ ላይ ባደረገው ንግግር እንደገለፀው የምሳ ግብዣ ወጪውን የቻለውን ወጣት ዮርዳኖስ ካሳን ጨምሮ በማዕከሉ በዓሉን ለማክበር የተገኙትን ድምጻዊ ብርሃኑ ተዘራ ፣ አርቲስት ናርዶስ አዳነ እና አርቲስት ማስተዋል ወንደሰን አመስግኗል። ማዕከሉን የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድጋፍ የሚሻ በመሆኑ በተቻለው አቅም ሊታገዝ እንደሚገባ አሳስቧል።

ጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከል በ1998 ዓ.ም ተቋቁሞ ከኢፌድሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ፈቃድ አግኝቶ በአዕምሮ ሕመምና በተለያዩ ደዌ ታመው በሚሰቃዩ ሕሙማን ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራ አገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፤ ዓላማውም ምንም ዓይነት ጧሪ ቀባሪ ለሌላቸው የአዕምሮ ሕሙማን ምግብ፣ መጠለያ እንዲሁም አስፈላጊውን ሕክምና እንዲያገኙ በማድረግ የተሟላ ቤተሰባዊ ፍቅርና እንክብካቤ በመስጠት ላይ የሚገኝ በጎ አድራጎት ተቋም ነው።

ማዕከሉ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከ1000 በላይ የአዕምሮ ህሙማንና በተለያየ ደዌ ታመው የሚስቃዩ ህሙማንን ከጎዳና እና ከተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት በር ላይ በማንሳት በተከራየው የሕሙማኑ ማገገሚያ ማዕከል ውስጥ በማስገባት አስፈላጊውን መሰረታዊ ፍላጎታቸውን በሟሟላት ላይ ይገኛል።

የጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ እና ማገገሚያ ማዕከልን ለመደገፍ 6860 ላይ ok ብለው በመላክ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000003785495 ማገዝ ይችላሉ።

59540cookie-checkመልካም የበጎ አድራጎት ተግባር

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE