የጎጆ ብሪጅ ሁለተኛውን የጤና ዘርፍ እና መደበኛው የጎጆ ሮስካ ዕጣ አወጣ።

Reading Time: 2 minutes
ሁለተኛው ዙር የጤናው ዘርፍ እና መደበኛ የማህበረሰቡ የጎጆ ሮስካ እጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ ጳጉሜ 5 ቀን 2015 ዓም በግራንድ ኤሊያና ሆቴል በተካሄድ የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት በጤና ዘርፍ ለ200 እድለኞች እጣ የወጣ ሲሆን በመደበኛ ሮስካ ደግሞ 300 እድለኞች የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ተካሄዷል።

በዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓቱ ላይ የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች፣ የጎጆ ብሪጅ ሀውስ የቦርድ አባላት፣ የዳሽን ባንክ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም በርካታ የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ደንበኞች ተገኝተዋል።

የጎጆ ብሪጅ ሀውስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አልማው ጋሪ በዛሬው ዕጣ ማውጣት መርሃግብር ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት የእጣ አወጣጥ ስነስርአት እጅግ በጥንቃቄ እና ሀላፊነት በተሞላበት፣ ተጠያቂነት በሰፈነበት መንገድ እንዲካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ከተለያዩ አጋር ተቋማት ጋር በመቀናጀት ሲሰራ መቆየቱን
የገለጹ ሲሆን በተለይ 2ኛ ዙር የጤናው ዘርፍ እና መደበኛ የማህበረሰብ የጎጆ ሮስካ ዕጣ ተመዝጋቢዎች በትዕግስት እጣው እስከሚወጣበት ቀን ድረስ በመጠበቃቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ጎጆ ብሪጅ እስካሁን ስምንት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ማህበራትን ያደራጀ ሲሆን አንዱ ማህበር ግንባታ መጀመሩ ተገልጿል። ሌሎች የክረምት ወቅት ለግንባታ መጀመር አመቺ ስላልሆነ በቀጣይ እንደሚጀምሩ ተገልጿል። በጤና ዘርፍ የወጣው የመጀመሪያው ዙር እድለኞች የማህበር ማደራጀት ስራው እየተሰራ እንደሆነ ተገልጻል።

በቀጣይ የክፍያ መቆጣጠሪያ ሶፍትዌር እየበለፀገ እንደሆነ የገለፁት የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አልማው ጋሪ በቀጣይ ከዋጋ መጨመር ጋር ተያይዞ ጥናት እየተጠና ሲሆን መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ እንደሚኖር ተናግሯል።

የጎጆ ብሪጅ ሀውሲንግ 3ኛ ዙር የጤናው ዘርፍ እና መደበኛ የማህበረሰቡ የጎጆ ሮስካ ዕጣ ከ 3 ወር በኋላ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

59480cookie-checkየጎጆ ብሪጅ ሁለተኛውን የጤና ዘርፍ እና መደበኛው የጎጆ ሮስካ ዕጣ አወጣ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE