ያኔት ኮሌጅ በጤና እና ቢዚነስ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

ያኔት ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ለ14ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዲኘሎማ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በሁለተኛ ዲግሪ ዛሬ ነሐሴ 28 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው የኦሮሚያ ባህል ማዕከል አስመርቋል።


የምረቃ ሥነ ሥርአት ላይ ዶ/ር ዮሐንስ ጫላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም እንዲሁም አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ በአዲስ አበባ ቢሮ ኃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ሥራ አስኪያጅና የአገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ በተገኙበት የምርቃት ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።

በደረጃ 4 አካውንቲንግና ፋይናንስ፣ በሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ በነርሲንግና ፋርማሲ በመጀመርያ ዲግሪ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ፣ በሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ፣ በክሊኒካል ነርስ እና በሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ ፕሮግራም) ማስተርስ ኦፍ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን፣ ማስተርስ ኦፍ ፐብሊክ ሄልዝ አስመርቋል፡፡

ከፍተኛ ነጥብ ያመጡ ተመራቂዎች የዋንጫ እና የሜዳሊያ ተሸላሚም የሆኑ ሲሆን የዘንድሮ ተመራቂዎች አብላጫ ውጤት ያመጡት ሴቶች መሆናቸው እንዲሁም የሁለተኛ ዲግሪ (ማስተርስ) ተመራቂ ተማሪዎች የሜዳሊያ ተሸላሚዎቹ ተመሳሳይ (አንድ ዓይነት) ነጥብ በማምጣት ግጥጥሞሹ አስገራሚ እንዲሆን አድርገውታል፡፡

በዛሬው እለት በኦሮሞ ባህል ማእከልም በተደረገው የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የ2015ዓ.ም የመውጫ ፈተና በተለይም በጤናው ዘርፍ በክሊኒካል ነርስ 61 በመቶ ፣ በሜዲካል ላብራቶሪ 50 በመቶ ተማሪዎችን ማሳለፍ መቻሉና በቀጣይም የትምህርት ጥራት ደረጃን በማሳደግ ከዚህም በላይ ለመስራት ዝግጅት ማድረጉን የኮሌጁ ዲን ረ/ፕሮፌሰር ሳሙኤል ደሱ ተናግረዋል።

ያኔት ኮሌጅ ከሰፈረ ሰላም ካምፓስ በተጨማሪ በ6 ኪሎ ቅርንጫፍ ያሬድ ሙዚቃ ትትምህርት ቤት አጠገብ በሚገኘው ካምፓስ ክሊኒካል ፋርማሲ፣ በክሊኒካል ነርስ እና ማርኬቲንግ ማኔጅመንት በመጀመሪያ ዲግሪ እውቅና ወስዶ በማስተማር ላይ ሲገኝ በሁለተኛ ዲግሪ በማስተርስ ኦፍ ፐብሊክ ኸልዝ በ 2016ዓ. ም መስከረም ወር ላይ ምዝገባ እንደሚጀምር የኮሌጁ መስራችና ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዳዊት ጌታቸው በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ተናግረዋል::

በስተመጨረሻም ዶ/ር ዮሀንስ ጫላ የአ/አ ጤና ቢሮ ኃላፊ ለተመራቂ ተማሪዎች የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

ፎቶ፦ ቴድ ካሳ

59160cookie-checkያኔት ኮሌጅ በጤና እና ቢዚነስ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE