“መስሪያ ቤት”የተሰኘ አዲስ ሲትኮም ድራማ በሳምንት ሁለት ቀን በካናልፕላስ ቻናል 2 ላይ ከጳጉሜ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ መቅረብ ሊጀምር ነው።
ካናል ፕላስ “መስሪያ ቤት” ከተሰኘው ሲትኮም ድራማ ባሻገር ከመስከረም 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ “የእውቀት ዛፍ” የተሰኘ ከ3 እስከ 10 ዓመት ለሆኑ ልጆች ታስቦ የተዘጋጀው ትምህርታዊ ፕሮግራም በካናል ፕላስ ድክድክ ላይ እንደሚተላለፍ የኔ ቫይብ “መስሪያ ቤት”የተሰኘውን አዲስ ሲትኮም ድራማ ለመመረቅ በዓለም ሲኒማ በተከናወነው መርሐግብር ላይ ሰምቷል።
ካናል ፕላስ ከ40 በሚበልጡ የአውሮፓ፣ የእስያ ፣ ፓሲፊክ እና የአፍሪካ ሀገራት በመስራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን ከ 22 ሚሊዩን በላይ ደንበኞችን ማፍራት የቻለ የአለማችን ግዙፍ የክፍያ ቴሌቪዥን አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት ነው፡፡
ካናል ፕላስ በራሱ የሚያጋጃቸው ከ6ዐ በላይ የስርጭት ቻናሎች ያሉት ሲሆን በደረጃቸው የላቁ የሀገር ውስጥ እና ሌሎች አለም አቀፋዊ ቻናሎችንም በተለየ ዝግጅት ያቀርባል፡፡ ካናል ፕላስ ላለፉት 30 ዓመታት የክፍያ ቲቪን ለሀገሬው ባህሎች እና ቋንቋ እንዲስማማ አድሮ የቅረጽ አቅሙን እያስመሰከረ ስኬትን ሲያስመዝግብ ቆይቷል። በሀገራችን ስራውን ከጀመረ ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን በራሱ የሚያዘጋጃቸውን ልዩ ቻናሎቹን ወደ 14 አሳድጓል።
ካናል ፕላስ ኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ በራሱ የሚያዘጋጃቸውን በአማርኛ ቋንቋ የሚቀርቡ አስር ልዩ ቻናሎች እና እራት በኦሮምኛ ቋንቋ ተወዳጅ ቻናሎችን በድምሩ (14) የመዝናኛ ቻናሎችን የኢትዮጵያዊያ ተመልካቾችን ፍላጎት ሳቢ በማድረግ አዘጋጅቷል።
በተጨማሪም ካናል ፕላስ ኢትዮጵያ በርካታ የኢትዮጵያ ቲቪ ቻናሎች እና ራዲዮ ጣቢያዎችን ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ጥራቱ የላቀ ስርጭት ያቀርባል፡፡ ከነዚህም መካከል ኢ.ቢ.ኤስ፣ ቃና፣ ፋና ቲቪ፣ ኢቲቪ፤ አማራ ቴሌሺዥን ፤ ናሁ ፤ እሻም ፤ ኦ.ቢ.ኤስ ፤ ዋልታ ፤ እና ቲቪ ናይን እንዲሁም ሌሎች ይገኙበታል፡፡
583800cookie-checkካናል ፕላስ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ሊጀምር ነው።no