በ200 ሚልየን ብር ወጪ ተገዝቶ የተገጣጠመ የዲጅታል ማስታወቂያ ስክሪን ተመረቀ

Reading Time: 2 minutes
ኢሳያስ ማስታወቂያ ከሁለት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ አራት ኪሎ አደባባይ አካባቢ ዝግጁ ያደረገውን  የዲጂታል ማስታወቂያ ስክሪን ዛሬ ወደ ስራ እንዲገባ አድርጓል፡፡

በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ ከከተማ አስተዳደሩ የተወከሉ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተው ነበር፡፡

ድርጅቱ በከተማ አስተዳደሩ ባገኘው የማስታወቂያ ቦታ ከሁለት መቶ ሚሊዬን ብር በላይ ዘመናዊ የዲጅታል ማስታወቂያ ስክሪን አራት ኪሎ አደባባይ ላይ አስገጥሞ ለአገልግሎት ብቁ ምድረጉን አስታውቋል።

ኢሳያስ ማስታወቂያ ስራዎች በሃገሪቱ ካሉ ጠንካራ የማስታወቂያ ስራ ድርጅቶች መካከል አንዱ ሲሆን በርካታ የማስታወቂያ ስራዎችን በመስራት የሚታወቅ መሆኑ በመርሐግብሩ ላይ ተነስቷል።

ኢሳያስ ማስታወቂያ የዲጅታል ማስታወቂያ ስክሪን ባሁኑ ሰአት አራት ኪሎ ላይ ያስገጠመ ሲሆን በከተማው በ25 ቦታዎችም ለመግጠም መዘጋጀቱን ተናግሯል።

በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዳሬክተር አቶ ዳዊት ሁንዴሳ፣ ዘመናዊ የሆኑ የመልእክት ማስተላለፍያዎች የከተማዋን ውበት ከመጠበቅ አንጻር ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።

በሌላ መልኩ ደግሞ መልእክቶች ባልተገባ መንገድ እንዳይተላለፍ ቁጥጥሩን ማጥበቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

ዘመናዊ ከተማ ለመገንባት ዘመናዊ የመልእክት ማስተላለፍያዎች ሊኖሩ ይገባል ያሉት ዳሬክተሩ፣ ሌሎችም ተመሳሳይ ድርጅቶች ይህንን መንገድ እንዲከተሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ኢሳያስ ማስታወቂያ ከሚሰራቸው የማስታወቂያ ፣ የህትመትና የጋርመንት ስራዎች በተጨማሪ ደግሞ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ደግሞ ኢሳያስ ፋውንዴሽን የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት መስርቶ ለአርባ እናቶችና ህፃናት ላለፉት አስር ዓመታት የመጠለያ ፣የምግብና የትምህርት ቁሳቁስ እገዛ በማድረግ ላይ ይገኛል።

ኢሳያስ ማስታወቂያ በበርካታ ሀገራዊ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይም የጎላ ተሳትፎ በማድረግ የማይዘነጋ አሻራ አስቀምጧል።

58360cookie-checkበ200 ሚልየን ብር ወጪ ተገዝቶ የተገጣጠመ የዲጅታል ማስታወቂያ ስክሪን ተመረቀ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE