ኤለን መስክ በሰጠው ምለሽ የፌስቡክ መስራቹ ማርክ ዙከርበርግን “ፈሪ” ብሎታል
የሁለቱ አሜሪካዊያን ፍልሚያ የብዙዎችን ትኩረት የሳበ ሲሆን ባሳለፍነው አርብ ፍልሚያው በጣልያን መዲና ሮም እንደሚካሄድ ተገልጾ እንደነበር ይታወሳል።
ይሁን እንጂ የፌስቡክ መስራቹ እና የሜታ ክባንያ ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ ትሬድስ በተባለዉ አዲሱ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው ጽሁፍ፤ ኤለን መስክ ስለ ቦክስ ፍልሚያው የሚያወራዉ የምሩን አይደለም፤ ሰለዚህ ብንተወው ሳይሻል አይቀርም ብሏል።
ዙከርበርግ “ኤለን ቀን ሊቆርጥ አልቻለም፤ አንዴ ቀዶ ጥገና ያስፈልገኛል ይላል፤ አንድ ጊዜ ደግሞ እኔ ቤት ጓሮ የሙከራ ድብድብ እናድርግ ይላል” ሲል ቅሬታዉን ተናግሯል።