የዩክሬን ጎረቤት የሆነችው ፖላንድ ብዙ ዜጎች የተጠለሉ ሲሆን በሃገሬው ሴቶች ግን እንደ ስጋት እየታዩ ይገኛሉ።
በዚህ የተነሳ የፖላንድ ሴቶች ዩክሬናዊያን እንስቶች ባሎቻችንን ሊወስዱብን ይችላሉ የሚለው ስሜት እየተበራከተ መምጣቱ ነዉ የተሰማዉ።
ይህ በዚህ እንዳለ ግን ወጣት ዩክሬናዊያንን የሚፈልጉ ፖላንዳዊያን ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ተገልጿል። በተለይም በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ ወጣት ዩክሬናዊያን ሴቶችን የሚፈልጉ ማስታወቂያዎች በስፋት እየተሰራጩ ነውም ተብሏል።
ከወራት በፊት ወደ ብሪታንያ ያመሩ ዩክሬናዊያን የሰው ባል ቀምተዋል በሚል በማህበራዊ ሚዲያ ትችቶችን ማስተናገዳቸው ለስጋታቸዉ መባባስ አንድ ምክንያት ሆኗል ነዉ የተባለዉ።