በአፍሪካ የመጀመሪያው ሊትየም ማዕድን የሚያወጣ ማሽነሪ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ ነው።

Reading Time: 2 minutes
ቀንጢቻ ማይኒንግ ዛሬ ነሐሴ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ከ150 ሚሊዮን ብር ወጪ የወጣበት እና በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነው ሊትየም ማዕድን የሚያወጣ ” ዲኤም ኤስ ኘላንት 2022 “የተሰኘ ማሽን በቀጣይ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገባ የቀንጢቻ ማይኒንግ ባለድርሻ አካላት በጋራ ከሳውዲ በቀጥታ በሰጡት መግለጫ አሳውቀዋል።

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ደርሚ ዳማ ወረዳ ቀንጢቻ አካባቢ የሚገኘው የቂንጢቻ ማይንግ የተሰኘ የማአድን አውጪ ድርጅት መስራች እና ከፍተኛ ሼር ሄልደር የሆኑት ሀጂ አሊ ሁሴን በመግለጫው እንደገለጹት በአፍሪካ የመጀመሪያው ሊትየም ማዕድን የሚያወጣ ማሽነሪ በቀጣይ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ የሚገባ ሲሆን ይህ እንዲሳካ ለአደረጉ የመንግስት ተቋማት ፣ ለተለያዩ አጋር አካላት እና ግለሰቦች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ሊትየም በአለም ላይ እጅግ ተፈላጊ የማዕድን ዘርፍ ሲሆን
ይህ የማዕድን ዘርፍ በተለይ ለኤሌክትሪክ መኪናዎች ፣ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ ለኬሚካሎች፣ለፋርማሲዩቲካል እና ሊቲየም አየን ባትሪዎች በጥሬ እቃነት የሚያገለግል ሲሆን በኢትዮጵያ በብዛት የሚገኝ የማዕድን ዘርፍ መሆኑን
የቂንጢቻ ማይንግ ሌላኛው ሼር ሄልደር እና የኩባንያው የቦርድ አባል አቶ ሳሙኤል ሚሊዮን ገልጸዋል።

ቀንጢቻ ማይኒንግ አጠቃላይ እያከናወነ ስላለው ስራ የፊታችን ማክሰኞ በሸራተን አዲስ ሆቴል ዝርዝር ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ሼር ሄልደሮቹ ገልጸዋል።

(ጌች ሐበሻ)

57380cookie-checkበአፍሪካ የመጀመሪያው ሊትየም ማዕድን የሚያወጣ ማሽነሪ ወደ ኢትዮጵያ ሊገባ ነው።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE