አርቲስት አብረሃም ወልዴ እና ወ/ሮ ማክዳ ሀይለ ሚካኤል ለሰርጋቸው ወጪ በሚል በጎፈንድሚ እና በተለያየ መንገድ ከተሰበሰበው ከ2.2 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ውስጥ በድህነት ምክንያት ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን በዣ ወረዳ ለሚሰራው የጋበር በጎ አድራጎ ድርጅት እና በኦሮሚያ ክልል በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ዞን በፍቼ ከተማ የሚገኘውና ተማሪዎችንና አረጋውያንን በመመገብ ፣ የትምህርት ቁሳቁስ በማድረስ ላይ የሚሰራው ለፍቅር የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ማህበር ለእያንዳንዳቸው የ250ሺህ ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን በደብረብርሃን ለሚገኙ ተፈናቃዮች የሚውል 4ሺህ ብር እንዲሁም በዋግምራ ዞን ውስጥ ለ3 ወረዳዎች ለሚገኙ ከ30 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች የ1ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ለግሰዋል።

ጥንዶቹ ከዚህ ቀደም 300 ሺ ብር ለሜቄዶኒያ የአረጋዊያንና የአዕምሮ ህሙማን ማዕከል መለገሳቸው የሚታወስ ሲሆን ለሰርጋቸው ከሰበሰቡት 2 ሚሊዮን 266 ሺህ 205 ብር ከ56 ሳንቲም ውስጥ በጎፈንድሚ የተሰበሰበው 31 ሺ 935 .20 ዶላር ሲሆን፤ ቀሪው ገንዘብ በብር የተሰበሰበ መሆኑን በዛሬው መግለጫ ላይ አሳውቀዋል።

በገንዘብ ስጦታው ላይ ተገኝተው ምስጋና ያቀረብት
የሰቆጣ ዋግኸምራና የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ በርናባስ አርቲስቱ ከነባለቤታቸው እንዲሁም የሙያ አጓሮቻቸው እና እርዳታውን ለአደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
567400cookie-checkአርቲስት አብረሃም ወልዴ እና ወ/ሮ ማክዳ ሀይለ ሚካኤል የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ!no