«ለበለጠ አረንጓዴ ዘመን!» በሚል መሪ ሀሳብ ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ጊዜ የችግኝ ተከላ ኘሮግራም አከናወነ።

Reading Time: 2 minutes
የቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ ሠራተኞች እና የተቋሙ አመራሮች ከኢትዮጵያ የቅርስ ባላደራ ማህበር እና ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በጋራ በመሆን ዛሬ ሐምሌ 27 ቀን 2015 ዓ.ም በእንጦጦ ተራራ «ለበለጠ አረንጓዴ ዘመን» በሚል መሪ ቃል ለአምስተኛ ጊዜ የችግኝ ተከላ ኘሮግራም አከናወኑ።

የቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ ሠራተኞች እና የተቋሙ አመራሮች
ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር በየአመቱ ችግኞቹን መትከል ብቻ ሳይሆን የተተከሉትን ሙሉ የሚንከባከቡ ባለሙያዎችንም ጭምር በኢትዮጵያ ቅርስ ባለ አደራ ማህበር በኩል በቅጥር እንክብካቤ በማድረጋቸው ባለፉት ሶስት አመታት ውስጥ የተተከሉት ችግኞች ከ85በመቶ በላይ መጽደቃቸውን የቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ገብረስላሴ ስፍር በስፍራው ለተገኙ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማህበር ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ መቆያ ማሞ እንዳብራሩት «በቢ. ጂ . አይ ኢትዮጵያ » ከዚህ ቀደም በአራት ዙር የተከላቸውን ችግኞች በኃላፊነት ተረክቦ እንክብካቤ በማድረግ ላይ ሲሆን ማኀበሩ የተፈጥሮ ቅርስ የሆነውን የእንጦጦ ፓርክ ይዞታውን ጠብቆ ይኖር ዘንድ በመልካም ፈቃዳችሁ ከዚህ ቀደም ችግኞችን በመትከል አደራ የሰጣችሁን አካላት በሙሉ የሰጣችሁንን አደራ ጠብቀን ችግኞቻችሁን ተንከባክበን አሁን ባሉበት ይዞታ ላይ የደረሱ ሲሆን በቀጣይ በዚህ በያዝነው ክረምት ኀብረተሰብ ችግኝ እንዲተክሉ እና እንክብካቤ እንዲያደርጉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ቢ.ጂ. አይ ኢትዮጵያ በእንጦጦ ተራራ ላይ በርካታ ማኀበራዊ ኃላፊነቶችን እየተወጣ ሲሆን ይገኛል በተለይም ከዚህ ቀደም በእንጦጦ ፓርክ ውስጥ እንጨት በመልቀም ለሚተዳደሩ እናቶች የስንቅነሽ ሱቅ ያበረከተ ሲሆን በተከታታይ አምስት አመታት ደግሞ በእንጦጦ ፓርክ ሀገር በቀል ችግኝ በመትከል በኩል ትልቅ ድርሻ እያበረከተ ይገኛል ።

(ጌች ሐበሻ)

56590cookie-check«ለበለጠ አረንጓዴ ዘመን!» በሚል መሪ ሀሳብ ቢ.ጂ.አይ ኢትዮጵያ ለአምስተኛ ጊዜ የችግኝ ተከላ ኘሮግራም አከናወነ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE