ሐመር ተሪሸሪ ሆስፒታል የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን አበሰረ።

Reading Time: 2 minutes
በ2030 ዓ.ም ወደ ውጭ የሚሄደውን ህክምና ሙሉ
በሙሉ አስቀርቶ ማየት እንዲሁም በአይነቱም ሆነ በይዘቱ ከምስራቅ አፍሪካ ቁጥር አንድ ተመራጭ ተርሸሪ ሆስፒታል ሆኖ ማየትን ራዕይን አንግቦ የተመሠረተው ሐመር ተሪሸሪ ሆስፒታል የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን ዛሬ ሐምሌ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ለመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳወቃል።

አክሲዮን ማህበሩ በ17 የህክምና ባለሙያዎች አደራጅነት የተቋቋመ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገነባው ሆስፒታል   አጠቃላይ ወጪው  ሁለት  ነጥብ  አምስት ቢሊዮን ብር እንደሆነ አክሲዮን ማህበር አደራጅ የቦርድ ፕሬዝዳንት ዶክተር ዳንኤል አዱኛ የገለጹ ሲሆን ሆስፒታሉ  ከስድስት ወር በኋላ በኪራይ ህንፃ ላይ ስራ እንደሚጀምር ገልጸዋል።

የአክሲዮን ሽያጩ የፊታችን ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ በአማራ ባንክ ፣ በአዋሽ ባንክ በአቢሲኒያ ባንክ እና በዳሽን ባንክ  ሽያጭ የሚጀምር ሲሆን ለአንድ ወር ያክል አክሲዮን ለሚገዙ የመስራችነት እድል እንደሚያገኙ ዶክተር ዳንኤል አዱኛ ጨምረው ገልጸዋል።

በ 34 ሚልየን ብር በተከፈለ  ካፒታል የተመሰረተው አክሲዮን ማህበር ፤ የአንድ አክስዮን ዋጋው 1,000 ብር ሲሆን  መግዛት የሚቻለው ትንሹ  የአክስዮን ብዛት ሃምሳ ሲሆን ትልቁ  ደግሞ መቶ ሺህ አክስዮን መሆኑን አደራጅ ኮሚቴው አሳውቀዋል።

56290cookie-checkሐመር ተሪሸሪ ሆስፒታል የአክሲዮን ሽያጭ መጀመሩን አበሰረ።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE