ቤስት ዌስተርን ፕሪሚየር ዳይነስቲ ሆቴል በነገው እለት ይመረቃል።

Reading Time: 2 minutes
ሰባት አመታት በግንባታ ላይ የነበረው ቤስት ዌስተርን ፕሪሚየር ዳይነስቲ ሆቴል ነገ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ጥሪ የተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ፣ የተለያዩ ሀገራት ኤምባሲዎች፣ የአፍሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ተወካዮች ፣ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች፣ የሲቪክ ተቋማት አመራሮች በተገኙበት እንደሚመረቅ ዛሬ ጠዋት በሆቴሉ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የሆቴሉ ባለንብረቶች አሰውቀዋል።

ቤስት ዌስተርን ፕሪሚየር ዳይናሲቲ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል አገልግሎት እንዲሰጥ ታስቦ የአገራችን ሆቴልና ቱሪዝም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በቁጥርም ሆነ በጥራት ዓለም ዓቀፍ የሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ ከሚፈልገው አቅርቦት ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን በአዲስ አበባ ከተማ ወሎ ሰፈር አካባቢ ኢንሳ ፊት ለፊት የተገነባ ዓለም ዓቀፍ ሆቴል ነው።

ቤስት ዌስተርን ፕሪሜየር ዳይናሲቲ ሆቴል አለም አቀፍ እዉቅናን ካተረፉ ዝነኛ ሆቴሎች ግንባር ቀደም የሆነዉ ከ100 በላይ በሆኑ ሃገራት ውስጥ የሚገኝ ከ4700 በላይ ሆቴሎችን ከሚያስተዳድረዉ የቤስት ዌስተርን ሆቴሎች እና ሪዞርቶች አንዱ ሲሆን ሆቴሉ 89 በረንዳ ያላቸዉ ሰፋፊ ምቹ እና ዘመኑ ያፈራዉን መገልገያ የያዙ የመኝታ ክፍሎች፣ ሬስቶራንት፣ ላውንጅ፣ ባር፣ ካፌ፣ ኬክ ቤት፣ የስብሰባ አዳራሽ፣ የቤት ውስጥ መዋኛ ገንዳ፣ ጂም፣ ሳውና፣ ስቲም፣ ሞሮኮ ባዝ፣ ማሳጅ ጭምር አገልግሎት ይሰጣል ።

ቤስት ዌስተርን ፕሪሜየር ዳይናሲቲ ሆቴል በሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ቤተሰብ ፍቅር እና መተሳሰብን ተቀዳሚ የኑሮ መርሃቸዉ ባደረጉ 12 የአንድ ቤተሰብ አባላት የተገነባ እንደሆነ ተነግሯል።

(ጌች ሐበሻ)
????ከበደ መክብብ

55800cookie-checkቤስት ዌስተርን ፕሪሚየር ዳይነስቲ ሆቴል በነገው እለት ይመረቃል።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE