የተወዳጁ ድምጻዊ ክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) 47ኛ አመት የልደት ቀን አስመልክቶ በስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከበረ።
መርሐግብሩን ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት ያዘጋጁት በክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን አድናቂዎች የተመሰረተው ወደ ፍቅር ጉዞ ማህበር ሲሆን ላለፉት 10 አመታት በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በመስራት የድምጻዊውን ልደት በማክበር ላይ እንደሚገኝ የማኀበሩ ዋና ሰብሳቢ አቶ ምስክር ታደሰ ገልጸዋል።
ወደ ፍቅር ጉዞ ማህበር በስለ እናት በጎ አድራጎት ድርጅት ባዘጋጀው ኘሮግራም ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የማኀበሩ አባላት እና የድምጻዊው የቅርብ ጓደኞች ተገኝተዋል።
ስለ እናት በጎ አድራጎት ድርጅት ከ20 ዓመት በፊት በ1994 ዓ.ም የተመሠረተ አገር በቀል በጎ አድራጎት ማህበር ሲሆን ማህበሩ ለችግር የተጋለጡ እና የተጎዱ ህጻናትን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውን ለመታደግ የተቋቋመ ማህበር ነው፡፡ ስለ እናት ወላጅ የሌላቸውን እና ተጥለው የሚገኙ ህጻናትን መጠለያ በመስጠትና አስፈላጊውን መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን በማሟላት የሚያሳድግ ተቋም ሲሆን ማህበሩ በማዕከሉ ከሚያሳደጋቸው ህፃናት ውስጥ ከፊሉ ህጻናት የአዕምሮና የአካል ውስንነት (Special Needs) ያለባቸው ሲሆኑ የተለያየ ልዩ እንክብካቤ እየተደረገላቸው ይገኛሉ።
ስለ እናት በጎ አድራጎት ከ500 በላይ ችግረኛ ሴቶች ራሳቸውን እንዲችሉ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ በማድረግና የመንቀሳቀሻ ካፒታል በመስጠት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሴቶች ወደ ስራ እንዲገቡ ያስቻለ ሲሆን ከ4500 በላይ የሆኑ ህጻናትን በመንከባከብ ለቁም ነገር አብቅቷል።
ማኀበሩ ከአዲስ አበባ ውጪ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ማኀበሩን ለማገዝ ለሚሹ ሁሉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000237880556 ወይም በአካል መምጣት አዲስ አበባ ሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ በንብ ባንክ አጠገብ ባለው ከሁሌቡና ፊትለፊት በአካል በመምጣት ማገዝ የሚችሉ ይሆናል።
557800cookie-checkየድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የልደት በዓል በስለ እናት የበጎ አድራጎት ድርጅት ተከበረ።no
መርሐግብሩን ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በቅንጅት ያዘጋጁት በክቡር ዶ/ር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን አድናቂዎች የተመሰረተው ወደ ፍቅር ጉዞ ማህበር ሲሆን ላለፉት 10 አመታት በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎችን በመስራት የድምጻዊውን ልደት በማክበር ላይ እንደሚገኝ የማኀበሩ ዋና ሰብሳቢ አቶ ምስክር ታደሰ ገልጸዋል።
ወደ ፍቅር ጉዞ ማህበር በስለ እናት በጎ አድራጎት ድርጅት ባዘጋጀው ኘሮግራም ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የማኀበሩ አባላት እና የድምጻዊው የቅርብ ጓደኞች ተገኝተዋል።
- See also: የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ
ስለ እናት በጎ አድራጎት ከ500 በላይ ችግረኛ ሴቶች ራሳቸውን እንዲችሉ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ በማድረግና የመንቀሳቀሻ ካፒታል በመስጠት በርካታ ቁጥር ያላቸው ሴቶች ወደ ስራ እንዲገቡ ያስቻለ ሲሆን ከ4500 በላይ የሆኑ ህጻናትን በመንከባከብ ለቁም ነገር አብቅቷል።
ማኀበሩ ከአዲስ አበባ ውጪ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ።
ማኀበሩን ለማገዝ ለሚሹ ሁሉ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000237880556 ወይም በአካል መምጣት አዲስ አበባ ሳርቤት ቫቲካን ኤምባሲ በንብ ባንክ አጠገብ ባለው ከሁሌቡና ፊትለፊት በአካል በመምጣት ማገዝ የሚችሉ ይሆናል።
- See also: የግራንድ አፍሪካ ረን