« ማለፊያ » የተሰኘው የድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አልበም ለገቢያ ሊቀርብ ነው።

Reading Time: 2 minutes
የተወዳጁ ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል « ማለፊያ » የተሰኘው ሁለተኛው አልበም የፊታችን ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚወጣ ዛሬ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ .ም ፒያሳ በሚገኘው ሀገር ፍቅር ቲያትር ቤት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ድምጻዊው ብስራት ሱራፌል ከኤላ ቲቪ ጋር በቅንጅት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳወቁ።

« ማለፊያ » የተሰኘው አዲሱ የሙዚቃ አልበም ለመስራት አራት አመታትን የፈጀ ሲሆን የሙዚቃ አልበሙ ላይ በኢንዱስትሪው ውስጥ ስመ ጥር የሆኑ ባለሙያዎች በግጥም በዜማ እንዲሁም በቅንብር አሻራቸውን አሳርፏል።

በቅንብር እውቁ የሙዚቃ ባለሙያ አበጋዝ ክብረወርቅ ሺዎታ፣ ታምሩ አማረ፣ ሚኪ ሃይሌ፣ ሱራፌል የሺጥላ፣ ፋኒ ጊዳቦ፣ ስማገኙሁ ሳሙኤል የተሳተፉ ሲሆን በግጥም አለማየሁ ደመቀ፣ ፍሬዘር አበበ፣ ምልዕቲ ኪሮስ፣ ወንደሰን ይሁን፣ አብዲ ተሳትፈውበቷል።

ድምጻዊ ብስራት ሱራፌል ሁሉንም ዜማዎች የሰራ ሲሆን ከዚህም ሌላ ለበርካታ አንጋፋ እና ወጣት አርቲስቶች የግጥምና የዜማ ስራዎችን በመስራት እና በመስጠት የሚታወቅ ሲሆን ከነዚህ መካከል ድምዊት ኩክ ስብስቤ፣ ድምጻዊ ሄለን በርሄ፣ ድምጻዊ ቬሮኒካ አዳነ፣ ድምጻዊ ሐይማኖት ግርማ፣ ድምጻዊ ሃሌሉያ ተክለጻድቅ ፣ ድምፃዊ ያሬድ ነጉ እና ለእነዚህና ለሌሎች ለበርካታ አርቲስቶች ስራዎችን በመስጠት ይታወቃል፡፡

አልበሙን ለገቢያ ያቀረበው ኤላ ቲቪ በሙዚቃ ኢንደስትሪው ቀዳሚ ከሚባሉት ድርጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን የበርካታ ሙዚቃ ባለሙያዎችን ስራዎቻቸውን ወደ ህዝብ እንዲደርሱና ተደማጭ መሆን እንዲችል የድርሻውን እያበረከተ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን ከዚህም ባሻገር የሙዚቃ ስራ ባለሙያውን ተጠቃሚ ማድረግ በሚችል ሁኔታ በመስራት ይታወቃል፡፡

አዲሱ የሙዚቃ አልበሙ 12 ሙዚቃዎችን አካቶ የፊታችን ሐምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ይወጣል።

55330cookie-check« ማለፊያ » የተሰኘው የድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አልበም ለገቢያ ሊቀርብ ነው።

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE