አራተኛው አርኪ የሪል ስቴት ኤክስፖ በስካይ ላይት ሆቴል ተከፈተ
=======#=======
አርብ ታህሳስ 25 ቀን 2017
የቤት ሻጮችና ገዢዎች፣ እንዲሁም ገንቢዎች የተለያዩ ተቋማትን ለማገናኘትና ለማስተሳስር ዕድል ይሰጣል የተባለለት አራተኛው አርኪ ሆምስ ኤክስፖ በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል በይፋ ተከፍቷል።
ከዛሬ ታህሳስ 25 እስከ ታህሳስ 27/2017 በሚካሄደው በዚህ ኤክስፖ በርካታ የቤት አልሚዎች እየገነቡት ስላለው ቤት ግንባታዉ ያለበት ደረጃ፣ ሊገነቡት ስላቀዱት ቤት፣ ቤቶቹን ዋጋ፣ ስለሚፈልጉት እቃ እና አገልግሎት ከኤክስፖ ተሳታፊዎችና ከጎብኚዎች ጋር መረጃና ልምድ ይለዋወጣሉ ተብሏል።
ወቅቱ የበዓል እንደመሆኑ በርካታ ዲያስፖራዎች ወደ ሀገር ቤት የሚገቡ በመሆኑ የኤክስፖውን ሳይጎበኙ ቤት እንዳይገዙ በሚል ሙሉ ቅድመ ዝግጅት የተደረገበት ልዩ የገና በዓል ቅናሽ መኖሩም ተገልገልፃል።
አርኪ ኤቨንት ኦርጋናይዘር ያዘጋጀው ይሄ ኤክስፖ በዘርፉ ላይ የተሰማሩ የቤት አልሚ ድርጅቶች እና አጋር አካላት እንደሚሳተፉ የተገለፀ ሲሆን ኤክስፖው መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ፤ አንድ ላይ በማቀናጀት በከተማ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ ሊሰሩ የታሰቡ መዋቅራዊ ቅንጅቶችን ለመፍጠር ምቹ ዕድል የሚፈጥር ገዥና ሻጭን በአንድ ላይ በማገናኘት በቀጥታ የሚፈልጉትን የቤት ዓይነት የሚመርጡበት ስለአጠቃላይ ሂደት በግልፅ መረጃ የሚለዋወጡበት በርካታ አማራጮች ያሉበት ለተረጋጋና ምክንያታዊ የቤት ግዥ ዉሳኔ ምቹና ዓይነተኛ አጋጣሚ እንደሚፈጥር የዝግጅት ክፍሉ ያስታወቀ ሲሆን ሁሉም ቤት ገዥ እና አልሚ ይህ ዕድል ሳያመልጠዉ ኤክስፖዉን እንዲሳተፍ ጥሪ አቅረቧል፡፡