መንፈሳዊ የኦሮሞኛ ቻናልበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ-ጉባኤ ጥቅምት 1…

Reading Time: < 1 minute
*
መንፈሳዊ የኦሮሞኛ ቻናል

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ-ጉባኤ ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም  ውሳኔ መሰረት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ መገናኛ ብዙኃን ስርጭት ድርጅት በአዲስ መልክ ተደራጅቶ ወደ ሥራ አንዲገባና ተቋርጦ የነበረው ስርጭት አንዲቀጥል ተወስኗል።

ይህ ቴሌቭዥን ጣቢያ የቤተ ክርስቲያኒቷን ቀኖና፣ ዶግማና ትውፍቷን በጠበቀ መልኩ ሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ምዕመናትበራሳቸው ቋንቋ የቅዱስ ወንጌልን እንዲያገኙ ለማስቻል የተቋቋመ ሲሆን አሁን ከስምንት በሚበልጡ የሀገር ውስጥ ቋንቋዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

በተለይም በቋንቋ ምክንያት ከኦሮሚያና ከደቡብ የሀገራችን ክፍሎች የተበተኑ ምዕመናን ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን ለመሰብሰብ ብዙ ተግባራትን እየተደረገ አንደሚገኝ ይታወቃል። ይህም በማህበራት፣ በፅዋና በተለያዩ ማዕቀፍ ስር ሆናችሁ አገልግሎት እየሰጣችሁ የሚትገኙ ሁሉ ወንጌልን በሁሉም
ቋንቋ እንድናዳርስ ከኛ ጋር እንድትሰሩ ጥራያችንን እናቀርባለን።

በሌላ መልኩ ቴሌቭዥን ጣቢያው 24 ሰዓት በሰባቱንም ቀናት የሚሰራ በመሆኑ ሀገረ ስብከቶች በየሀገረ ስብከታችሁ ያለውን የልማት እንቅስቃሴና ሌሎች ሐዋርያዊ ተልዕኮን ከሳተላይቱ ላይ የዓየር ሰዓት በመውሰድ እንድትገለግሉበት ፣ እንዲሁም ታላላቅ የቤተ ክርስቲያናችን አገልጋዮች ሚዲያውን የሚያሳድጉ ምክረ ሀሳቦችን አንድትሰጡን እያልን ወደ ስርጭት የተመለሰውን  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ ቴሌቪዥን መገናኛ ብዙኃን ለማግኘት የሚከተለውን አማራጭ ይጠቀሙ።

Name: EOTC – AON
𝐅𝐫𝐞𝐪𝐮𝐞𝐧𝐜𝐲 𝟏𝟏𝟓𝟒𝟓 
𝐬𝐲𝐦𝐛𝐨𝐥 𝐫𝐚𝐭𝐞 45000 
𝐏𝐨𝐥𝐚𝐫𝐢𝐳𝐚𝐭𝐢𝐨𝐧 : 𝐇 
𝐅𝐄𝐂: 𝟓:𝟔
169460cookie-checkመንፈሳዊ የኦሮሞኛ ቻናልበኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ-ጉባኤ ጥቅምት 1…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE