ታላቅ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ በዓል “በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን፥ አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ፤ በዚያ…

Reading Time: < 1 minute
*
ታላቅ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ በዓል

“በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን፥ አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ፤ በዚያን ጊዜ በአሕዛብ ዘንድ፦ “እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገላቸው፡” ተባለ። እግዚአብሔር ታላቅ ነገርን አደረገልን፥ ደስም አለን።” መዝ 126 ፥3

    በሰሜን አሜሪካ በቨርጂንያ ግዛት በአሌክሳንደርያ ከተማ የሚገኘው የምስካየ ኅዙናን መድኀኔዓለም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተመሠረተ በጥቂት ዓመታት ውስጥ በፈቃደ እግዚአብሔር በዲሲ ፣ ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን የተዋሕዶ ልጆች ምዕመናን መጽናኛ የሚሆን ግዙፍ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን በ 3.1 Million USD ተገዝቶ የቁልፍ ርክክብ መደረጉ ይታወቃል።

     ስለሆነም ይህ ታላቅ ሕንጻ ቤተክርስቲያን የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጰጳሳትና ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ ሊቃውንት በተገኙበት የፊታችን ቅዳሜ ታኅሣስ 26/2017 ዓ.ም (Sat, Jan 04/2025) በሀገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 4:00PM ጀምሮ ቤተክርስቲያኑ ይባረካል።

እሁድ ታኅሣስ 27/2017 ዓ.ም (Sun, Jan, 05/2025) በሀገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 1:00 AM ጀምሮ ሥርዓተ ማኅሌቱና የቅዳሴ ቤቱ በዓል ስለሚከበር ከላይ በተጠቀሱት ታሪካዊ ቀናት የተዋሕዶ ልጆች ምዕመናን ሁላችሁም በቦታው  (2912 King St Alexandria VA 22302) ተገኝታችሁ በዓሉን እንድታከብሩ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን ::

ሰላመ እግዚአብሔር አይለየን
    መልአከ ገነት ቀሲስ ጥላሁን አበበ
              የደብሩ አስተዳዳሪ
169430cookie-checkታላቅ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ በዓል “በዚያን ጊዜ አፋችን ደስታን፥ አንደበታችንም ሐሴትን ሞላ፤ በዚያ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE