7ኛው አመታዊ ኢቲ ሪል እስቴት ኤክስፖ ተከፈተበዛሬው እለት 7ኛው አመታዊ ኢቲ ሪል እስቴት እና የቤት ኤክስ…

Reading Time: < 1 minute
*
7ኛው አመታዊ ኢቲ ሪል እስቴት ኤክስፖ ተከፈተ

በዛሬው እለት 7ኛው አመታዊ ኢቲ ሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ በሻራተን ሆቴል የመክፈቻ ዝግጅቱን ያደረገ ሲሆን እስከ እሁድ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የግሉ የቤት ልማት ዘርፍ የሚኖረውን ሚና ለማሳደግ እንዲረዳ ታስቦ መዘጋጀት የጀመረው ኢቲ ሪል ስቴት እና ሆም ኤክስፖ የሪል ስቴት አልሚዎችን ከገዥዎች፣ ከሻጮችና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የሚያገናኝ ኤግዚቢሽን መሆኑ ተገልጿል።

በዝግጅቱ መክፈቻ ላይ በተደረገው ውይይት ሪል ስቴቶች በታሰበው ፍጥነት እድገት እንዳያስመዘግቡ ተግዳሮቶች መኖራቸውንና ከእነሱም ውስጥ የፋይናንስ እጥረት እና የረጅም ጊዜ የብድር አገልግሎት ህግ አለመኖር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በመሆኑም ለውጭ ሀገር ባንኮች ገበያው ክፍት መደረጉ መልካም ለውጥ ይዞ እንደሚመጣና ከውጪ ባንኮች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታ እንደሚፈጠር ተስፋ መኖሩን የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገልጸዋል፡፡

የመኖሪያ ቤት የዋጋ ንረትን የሚያስከትለው ሌላኛው ነገር የጥሬ እቃ እና የግንባታ እቃዎች የዋጋ ውድነት እንደሆነ እና ሁሉንም የማህበረሰብ አቅም ያማከለ ንድፍና ዋጋ ለማቅረብ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል የተለያዩ በግንባታ ስራ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በአንድ ላይ መሰብሰብ ተጠቃሚው የተሻለ አማራጮችን እንዲያገኝ እንደሚያደርግ የካዝና ግሩፕ ሊቀመንበር አዲስ አለማየሁ ጠቁመዋል፡፡

ኤግዚቢሽኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለመቅረፍ ወሳኝ የሆኑ ዘላቂ የግንባታ አሰራሮችን፣ ተመጣጣኝ የቤት መፍትሄዎችን እና የፋይናንስ አማራጮችን የሚያጎላ ነው የተባለለት ሲሆን ከመንግስት ተወካዮች እና ባለድርሻ አካላት በኤግዚቢሽኑ ተገኝተዋል፡፡
167110cookie-check7ኛው አመታዊ ኢቲ ሪል እስቴት ኤክስፖ ተከፈተበዛሬው እለት 7ኛው አመታዊ ኢቲ ሪል እስቴት እና የቤት ኤክስ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE