የጋሞ አባቶች ደማቅ የጀግና አቀባበል ተደረገላቸውየጋሞ አባቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀ…

Reading Time: < 1 minute
*
የጋሞ አባቶች ደማቅ የጀግና አቀባበል ተደረገላቸው

የጋሞ አባቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀው BIWs PRIZE ውድድር በሰላም ዘርፍ የ10 ሚሊዮን ብር እና የዋንጫ ሽልማቶችን አሸንፈው በጋሞ ዞን መዲና አርባ ምንጭ ከተማ ሲገቡ ደማቅ የጀግና አቀባበል አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አባይነህ አበራ በአርባ ምንጭ፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተሞች በተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል በዞኑ ህዝብና መንግሥት ስም ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የጋሞ አባቶች በሀገሪቱ ሰላምን ለማውረድ ከፈፀሙት ገድል አንፃል ሽልማቱ ሲያንሳቸው እንጂ አይበዛባቸውም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው አባቶቻችን የጋሞ ብቻም ሳይሆኑ የመላው ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያን አባቶች ናቸው ብለዋል።

ሰላም በሰማይ ብቻ ሳይሆን በምድርም ዋጋ አለው ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ሰላም በምድር ያላትን ዋጋ የጋሞ ዞን እያጣጣመው ይገኛል ብለዋል።

ክብር ለሚገባው ክብር መስጠት ተገቢ በመሆኑ ይህን ውድድር አዘጋጅተው በመሸለም እውቅና ለሰጡ አካላትም ምስጋናቸውን በዞኑ ህዝብና መንግሥትን ስም አቅርበዋል።

ከጋሞ አባቶች አንዱ የሆኑት ሁዱጋ ሰዲቃ ስሜ ድሉ የመላው የጋሞ አባቶች እና ባህላቸውናን እሴታቸውን እክብረው የአባቶቻቸው የሰላም ጥሪ ተቀብለውና ታዘው ሰላምን ያወረዱ የጋሞ ወጣቶች ጨምር መሆኑን በመናገር ባህላቸውን እንዲያስቀጥሉ አደራ ብለዋል።

የሰላም ተምሳሌቶችን የጋሞ አባቶችን ደማቅ አቀባበል ላደረጋችሁ አርባ ምንጭም አዲስ አበባ ያላችሁ በዞኑ መንግስት ስም ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

Via የጋሞ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽንስ
167080cookie-checkየጋሞ አባቶች ደማቅ የጀግና አቀባበል ተደረገላቸውየጋሞ አባቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በተዘጋጀ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE