አመታዊ የሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ ለሰባተኛ ጊዜ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉትን ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀ…

Reading Time: < 1 minute
*
አመታዊ የሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ ለሰባተኛ ጊዜ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉትን ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ከነገ ከታህሳስ 18, 19 እና 20 ቀን 2017 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ኢንተርናሽናል ሆቴል እንደሚካሄድ አዘጋጁ 251 ኮሙኒኬሽን ኤንድ ማርኬቲንግ ገልጿል።

አገራችን ኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ አዳጊ ኢኮኖሚ እያስመዘገበች ያለችበት ወቅት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፣ በዚሁ ረገድ በቤት ልማት ዘርፍ አያሳደገች ያለችውን እድገት ተከትሎ የግሉ ዘርፍ የሚኖረውን ሚና ለማሳደግ እንዲረዳ ታስቦ መዘጋጀት የጀመረው ኢቲ ሪል ስቴት እና ሆም ኤክስፖ የሪል ስቴት አልሚዎችን ከቤት ባለቤቶች፣ ከገዥዎች፣ ከሻጮች እና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የሚያገናኝ ቀዳሚ ኤግዚቢሽን እንደሆነ ተነግሯል።

በኤክስፖዉ ላይ በኢትዮጵያ የሪል ስቴት እና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ባለድርሻ አካላት ከፍተኛ አልሚዎችን፣ ባለሀብቶችን፣ የፋይናንስ ተቋማትን፣ የቤት ገንቢዎችን እና የቤተ ውበት ባለሙያዎችን ጨምሮ በአንድ ላይ ያሰባስባል የተባለ ሲሆንየ251 ኮሙኒኬሽን መስራች አቶ አዲስ አለማየሁ “የዘንድሮው ኤክስፖ በኢትዮጵያ ሪል ስቴት ዘርፍ ትልቅ ፋይዳ ያለው ክስተት ሲሆን በኢንዱስትሪው ውስጥ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸውን ተዋናዮችን ያሰባስባል። ዘላቂ ልማትን፣ ፈጠራን እና ኢንቨስትመንትን የሚያበረታታ መስተጋብራዊ መድረክ በመፍጠር የዘርፉን እድገት ለመደገፍ ቁርጠኛ ነን!” በማለት ማብራራቱ የሚዘነጋ አይደለም።

በ7ኛው አመታዊ ሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ ከኤግዚብሽኑ በተጨማሪ በኢንዱስትሪው ላይ ከሚገኙ ዋና ባለድርሻ አካላት እና ከመንግስት ተወካዮች ጋር የመገናኘት እድል የሚፈጥር ሲሆን በተጨማሪም የፓናል ውይይትም መሰናዳቱን ሰምተናል።
166900cookie-checkአመታዊ የሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ ለሰባተኛ ጊዜ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉትን ቅድመ ዝግጅቶችን በማጠናቀ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE