የትዝታው ንጉስ ጋሽ #ሙሐሙድ አህመድ ክብር እውቅና ስለ መስጠት…የአራት ዘመን ትውልድ አሻጋሪ ሙዚቀኛ ተወዳ…

Reading Time: < 1 minute
*
የትዝታው ንጉስ ጋሽ #ሙሐሙድ አህመድ ክብር እውቅና ስለ መስጠት…

የአራት ዘመን ትውልድ አሻጋሪ ሙዚቀኛ ተወዳጁ እና አንጋፋው ድምፃዊ የትዝታው ንጉስ ክቡር ዶ/ር ጋሽ #መሐሙድ #አህመድ የተለያዩ ክብር እንውቅና ሊሰጠው ነው፡፡

በትዝታ መሰላል አሻግሮ የበርካቶችን ልብ በትዝታ ማዕበል የሚያንሳፍፈው ዘመን አይሽሬ ጋሽ ሙሐሙድ አህመድ የክብር እውቅና ለመስጠት በዛሬ እለት አርብ ጥቅምት 23/2017 በሸራተን አዲስ ሆቴል በላሊበላ ላሊበላ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ፡፡

አድናቂዎቹ እና ወዳጆቹ በመሰባሰብ ኮሜቴ በማዋቀር ለአመታት በላይ ሰፊ ስራ እሰሩ እንደ ነበር ገልፀው ሰው በቁም ሳለ ማክበር ይገባናል፡፡

አምስት አበየት ክንውኖች ያሉት ለጋሽ ሙሐሙድ የመጨረሻ የሙዚቃ መድረክ ማዘጋጀት ማለት ያለበትን ሁሉ መምከር ያለበትን ሁሉ
በመጨረሻው ዝግጅት ይገልፃል ፣ የጋሽ ሙሐሙድ አህመድ ታሪክ የመፅሐፍ ምረቃ ፣ ጋሽሙሐሙድ አህመድ መንገድ/አደባባይ ማሰየም እና ለጋሽ ሙሐሙድ ሐውልት ማቆም ይገኙበታል ተብሏል፡፡

የጋሽ ሙሐሙድ አህመድ የመጨረሻ ሲዲ እና ከላይ የተጠቀሱት ሁሉ ለማጠናቀቅ ጥር 5/2017 ድረስ ይጠናቀቃል ብለዋል፡፡

ክብር ዶ/ር ጋሽ ሙሐሙድ በኢትዮጵያ ከ62 ዓመት በላይ ከልጅነት አንስቶ የአገራችን የሙዚቃ መድረክ የተለያዩ የአገራችንን ቋንቋ ተጫውቷል ከልጅነት እስከ እውቀት ድረስ ለ አስር አመታት የተለፋበት መፅሐፉም ጥር 3/2017 በሚልየም አዳራሽ በድምቀት ይመረቃል ለንባብም ይበቃል ተብሏል፡፡

via (ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ)
159680cookie-checkየትዝታው ንጉስ ጋሽ #ሙሐሙድ አህመድ ክብር እውቅና ስለ መስጠት…የአራት ዘመን ትውልድ አሻጋሪ ሙዚቀኛ ተወዳ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE