አሸዋ ቴክኖሎጂ ከ500 በላይ የዌብሳይት ቴፕሌት አበልፃጊዎችን አወዳድሮ ሊሸልም መሆኑን አስታወቀ።አሸዋ ቴክ…

Reading Time: < 1 minute
*
አሸዋ ቴክኖሎጂ ከ500 በላይ የዌብሳይት ቴፕሌት አበልፃጊዎችን አወዳድሮ ሊሸልም መሆኑን አስታወቀ።

አሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ ለረጅም ጊዜ ሲሰራበት የቆየዉን የቴክኖሎጂ ዉጤት ከ500 በላይ አበልፃጊዎችን በማሳተፍ ዘርፉን ለማበርታታት ፕሮጀክት ቀርፆ መንቀሳቀስ መጀመሩን በዛሬዉ ዕለት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታዉቋል።

የአሸዋ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳንኤል በቀለ ይህንን የፈጠራ ዉድድር በዘጠና ቀን ዘመቻ ወደስራ ስናስገባ የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን የቴክኖሎጂ እድገት ካለበት ደረጃ በአጭር ጊዜ የከፍታ ማማ ላይ ለማድረስ አልመን ነዉ ሲሉም ተናግረዋል፡፡

አቶ ዳንኤል አክለውም በመርሀገብሩ በቅድሚያ የተወዳዳሪዎች ምዝገባ የሚካሄድ ሲሆን ምዝገባዉም እስከ ኖቬምበር 8 ድረስ የሚካሄድ እንደሆነና በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚገኙ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ተማሪዎችን እንዲሁም በዘርፉ በግላቸው የሚንቀሳቀሱ ከ500 በላይ ዌብሳይት አበልፃጊዎችን አወዳድሮ እንደሚሸልም እንዲሁም ለወጣቶች የስራ ፈጠራ ሀሳባቸዉን ይዞ መምጣቱን ገልፀዋል።

ውድድሩ እስከ መቶ ሺህ ብር(100,000) ሽልማት እንደሚያስገኝም ተገልጿል በተጨማሪም የዌብ ዲዛይኑ ትኩረት አድርጎ የሚሰራባቸው የስራ ዘርፎች ኢኮሜርስ፣ቱሪዝም፣ሆስፒታሊቲ፣የሄልዝ ኬር፣የተማሪዎች ሰርቪስ፣የማህበረሰባዊ ትስስር ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ማወቅ ተችሏል፡፡

ይህም ፕሮጀክት ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር፤ ለአገር ዉስጥ የምጣኔ ሀብት እድገትና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር እንደሚችል እና አዳዲስ የኢኖቬሽን ስራዎች በማካተት ለዌብ ዲዛይኑ አለም አቀፋዊ ይዘት ያላቸዉ ተብሌኖችና ዲዛይኖች እንዲፈጠሩ ለማየት እንደሚያስችል ተነግሯል።
159240cookie-checkአሸዋ ቴክኖሎጂ ከ500 በላይ የዌብሳይት ቴፕሌት አበልፃጊዎችን አወዳድሮ ሊሸልም መሆኑን አስታወቀ።አሸዋ ቴክ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE