በሁለት አመት ውስጥ 1.5 ሚልየነር የማፍራት ፕሮጀክት ተጀመረ በላይ አትክልት እና አስቤዛ ማዕከል” የሚል…

Reading Time: < 1 minute
*
በሁለት አመት ውስጥ 1.5 ሚልየነር የማፍራት ፕሮጀክት ተጀመረ

በላይ አትክልት እና አስቤዛ ማዕከል” የሚልየነሮች መንገድ ” የተሰኘ ፕሮጀክት ይፋ ያደረገ ሲሆን በዚህም 1.5 ሚልየን በሀገር ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ንግድ የሚሰሩበት የባንክ አካውንት በማስከፈት ከትንሽ ብር ተነስተው በሁለት አመት ውስጥ ሚልየነር የሚሆኑበትን ስልጠናና ምክር በነጻ እሰጣለሁ ብሏል።

ስልጠናው የፊታችን ከጥቅምት 30 ጀምሮ በማህበራዊ ሚድያዎች በኤስ ኤም ኤስ መልዕክት እንዲሁም በሀገሬ ቲቪና በኢትዮ ኤፍኤም ራዲዮ በሚተላለፉ ፕሮግራሞች ላይ እንደሚሰጥ የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ አቶ በላይ ሞሪዳ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

እንደ ስራ አስኪያጁ ገለጻ ከሆነ ሰልጣኞች በስልጠናው ምንም ገንዘብ የማይከፍሉ ሲሆን መስራት የሚፈልጉትን ስራ እንዴት ማሳደግ እንዳለባቸው እንዴት ገበያ መፈለግ እንዳለባቸው እንዲሁም ሌሎች የንግድ አማራጮችን የሚማሩበትና በዚህ ስልጠና ስኬት ካገኙ ሰዎች ልምድ የሚቀስሙበት ነው ብለዋል።

እንደ ምሳሌነትም በ1500 ብር ተነስቶ አሁን ላይ ከ75ሺ በላይ ደንበኞችን ያፈራውን የአትክልትና የአስቤዛ መሸጫ ማዕከሉን አቶ በላይ እንደ ምሳሌነት አቅርቧል።
ምዝገባውና ስልጠናውም ባሉበት ሆነው በተለያዩ አማራጮች እንደሚመዘገቡ ገልጸዋል ።
159110cookie-checkበሁለት አመት ውስጥ 1.5 ሚልየነር የማፍራት ፕሮጀክት ተጀመረ በላይ አትክልት እና አስቤዛ ማዕከል” የሚል…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE