የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ

Reading Time: 2 minutes

ብላክ ዳይመንድ አድቨርታይዚንግ በሚል ስያሜ ለበርካታ አመታት የተለያዩ የህትመትና የማስታወቂያ ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኘው ድርጅት ብላክ ዳይመንድ አፍሪካ የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ በሚል ከወረቀት ህትመት ውጪ በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ በልዩነት የህትመትና የማስታወቂያን ትምህርትና ዕዉቀት ብቃትና ልምድ ባላቸው መምህራኖች በዘመኑ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ለማስተማር መዘጋጀቱን ተቋሙ በዛሬው እለት በሰጠው ጋዜጣው መግለጫ አሳውቋል።

የብላክ ዳይመንድ አፍሪካ የህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ መስራች አቶ ተስፋዬ ነጋሽ ከነገ መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም 22 በሚገኘው ቢሮ ለአንድ ሳምንት ምዝገባ እንደሚጀምርም ጭምርም ገልጸዋል።

ድርጅቱ ከአንድ ወር እሰከ ሶስት ወር ድረስ ለሚቆይ ጊዜ የባነር፣ የስቲከር ህትመት ማሽነሪ፣ ሲ ኤን ሲ ማሽነሪ፣ የሌዘር መቁረጫ ማሽነሪ፣ የህትመትና ግራፊክስ ዲዛይን፣ ላይት ቦክስ ማስታወቂያ፣ ኒዮን ላይት ማስታወቂያ፣ የማስታወቂያ ገጠማ፣ የማስተወቂያ ፕሮዳክሽን፣ እስቲከርና ባነሮች መለጠፍ፣ የኢንዶርና አውትዶር ማስታወቂያ ስራ፣ የማይካ ሪሊፍ ሙያ ላይም ስልጠና እንደሚሰጥ ገልጿል።
156100cookie-checkየህትመትና ማስታወቂያ ማሰልጠኛ አካዳሚ ተከፈተ

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE