የእጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)አሁናዊ መረጃ የተሰጠ::”ተወዳጇ ድምፃዊት ጂጂ የሕይወት ጥልፍልፍ ውስጥ ናት” ጋዜ…

Reading Time: < 1 minute
*
የእጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)አሁናዊ መረጃ የተሰጠ::

“ተወዳጇ ድምፃዊት ጂጂ የሕይወት ጥልፍልፍ ውስጥ ናት” ጋዜጠኛ ወንድወሰን ከበደ!!

👉በቅርቡ ወደ ሀገሯ ትመለሳለች ” ተብሎ ሲነገር የነበረው ከእውነታ የራቀ ነው”

ወንድወሰን ከበደ ከዋሽንግተን ስለ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው መልዕክት አስተላልፏል።

እኔና ጂጂ እዉቂያችን በ1987 አ.ም የሚጀምር ሲሆን በዚያን ግዜ የአስቴር አወቀና ፡የቡዙዬ ጥሩ አድርጋ ትጫወት ነበር ።

ብዙም ሳትቆይ ወደ አሜሪካን ሀገር ሀገር ሄደች ፡እሷ ከሄደች ከጥቂት አመታት በኋላም እኔም ወደ አሜሪካን ሀገር አቀናሁ የተለያየ ስቴት እንኖር ስለነበር ሳንገናኝ ቆየን ከአመታት በኋላ ከኒዮርክ አንድ ወዳጄ ያለችበትን ጥሩ ያልሆነ ሁኔታ ስለነገረኝ በስልክ እየተገናኘን ማውራት ያዝን

በየቀኑ በሚባል በስልክ እናወራለን ወደ ቀልቧ ስትመለስም በትዝታ የኢትጽያ የመድረክ ቆይታዋንም አንስተን እንጨዎወታለን ፡ተወዳጁ ድምፃዊ አያሌው መስፍንና፣ ሻምበል በላይነህን በስልክ አገናኝቻትም ተጨዎውተዋል።

ከጥቂት ወራት በፊት እሁድ ማለዳ ወደ ምትኖርበት ኒውዮርክ ብሮክስ ሁለት የሚዲያ ባልደረቦቼንና አንድ ወዳጄን አስከትዬ መንግስት በሰጣት ቤቷ ተገኝተን ተጨዎወትን ለሚወዳት ህዝብም በቪዲዮ መልክት አስተላልፋለች ፡ሆኖም በተለያየ ምክንያት እስክ አሁን ያለቀኩትን ቪዲዮ ከነምክንያቱና ተጨማሪ መረጃ ጋር የማጋራችሁ ይሆናል ።

ዛሬም ድረስ ጂጂ ወደ ሀገሯ ልትገባ ነው እየተባለ የሚነገረው ሁሉ ከሀቅ የራቀ ሲሆን ያለችበት ሁኔታ ህዝብ እንዳያቀው የሚደረገው ሴራም እጅግ ያሳዝናል።

ጂጂ ካለችበት የህይወት ጥልፍልፍ ወጥታ የምናይበት ቀን እንዲመጣ እግዚአብሔር ይርዳን።

ወንድወሰን ከበደ /ከዋሽንግተን
155430cookie-checkየእጅጋየሁ ሽባባው (ጂጂ)አሁናዊ መረጃ የተሰጠ::”ተወዳጇ ድምፃዊት ጂጂ የሕይወት ጥልፍልፍ ውስጥ ናት” ጋዜ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE