በመሬት መንሸራተት አደጋ የ10 ሰዎች ሕይዎት አለፈበሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ…

Reading Time: < 1 minute
*
በመሬት መንሸራተት አደጋ የ10 ሰዎች ሕይዎት አለፈ

በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2016 ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰው ሕይዎት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በአደጋው የ10 ሰዎች ሕይዎት አልፏል ያሉት የጠለምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋየ ወርቅነህ ናቸው።

ኀላፊው ከአሚኮ ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ የአራት ሰዎች አስከሬን በፍለጋ ተገኝቷል ብለዋል። የቀሪ ስድስት ሰዎች አስከሬን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሊገኝ አልቻለም ነው ያሉት።

በጉዳቱ በስምንት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል ያሉት ኀላፊው በደጃች ሜዳ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።

በመሬት መንሸራተት አደጋው ከ35 በላይ የቤት እንሰሳት ሞተዋል። ከ30 ሄክታር በላይ በሰብል የተሸፈነ መሬት ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

እንደ አቶ ተስፋየ መረጃ በደረሰው አደጋ 480 አባውራዎች እና 2 ሺህ 400 የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል። በቀበሌው ማዕከል ወደሚገኙ ማኅበራዊ ተቋማት በጊዜያዊ እንዲጠለሉ መደረጉንም ኀላፊው ጠቁመዋል።

ኀላፊው አያይዘውም በቀጣይም የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊከሰትባቸው ይችላሉ በተባሉ የኖላ፣ ላጌ፣ ውፋ፣ ኩዳድ እና ጅብ ዋሻ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

አሁን ካለው ከባድ የዝናብ ስርጭት አንጻር ማኅበረሰቡ ከጎርፍ እና መሰል አደጋዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ያሳሰቡት ኀላፊው ለተፈናቃዮች አፋጣኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት።

Via አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን
151320cookie-checkበመሬት መንሸራተት አደጋ የ10 ሰዎች ሕይዎት አለፈበሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE