አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃ እና ሳምንታዊ ሙዚቃዊ ጉዳይ በተጨማሪም በየሳምንቱ የምንጋብዛችሁ አልበም እንደ ተጠበቀ ሆኖ፡፡
– አፀደ ማርያም ያረጋል እና መቅደስ ዘውዱ-ሳብ ሳብ(እሱ የምለው) ፋና ላምሮቶቹ ፈርጥ የሆኑት ሁለቱ የባህል ሙዚቃ ድምፅ ተጫዋቾች ተጣምረው በዚህ ሳምንት ነጠላ ሙዚቃ ይለቃሉ፡፡ ግጥም እና ዜማ በተጨማሪ ፕሮዲውስ ያደረገው ድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ ቅንብር ሮቤል እንዳለ ሚክሲንግ ፍሬዘር ታዬ ማስተሪንግ አቤል ጳውሎስ በአቤል ሙሉጌታ ዩትዮብ ቻናል በቅርቡ ይደርሳል ተብሏል፡፡
– አሉላ ገብረ አምላክ- ”በመዋደዳችን” የድምፃዊ ቴዎድሮስ ታደሰን እንደ ገና እንደ አዲስ በአዲስ አቀራረብ ተጫውቶ ወደ ህዝብ ሊያደርስ ተዘጋጅቷል የዚህ ግጥም እና ዜማ ደራሲዎች አጋፋዎቹ በግጥም ይልማ ገብረዓብ ዜማ አበበ መለሰ በቢኤም ኢንተርቴመንት በኩል ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
-አብራት አብዱ”አሸንዳ” የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ ለ አድማጭ ታደርሳለች ይህንን ሙዚቃ ሐሙስ ምሽት በናሆም ሪከድስ በኩል ይደርሳል ተብሏል፡፡
-እመቤት ጌትነት- ”አሻሜ” የተሰኘ ነጠላ ሙዚቃ አሙስ ምሽት ለ አድማጭ ታደርሳለች ግጥም እና ዜማ ምስክር ምንዳዬ ቅንብር ሳሙኤል ዳንኤል ሰርቶታል በዳይሬክተርነት እራስዋ ድምፃዊ እመቤት ጌትነት ሰርታዋለች፡፡
– ዲጄ ግጥም እና ዜማ ደራሲ እንዲሁም አቀናባሪ ሮፍናን ኑሪ በባህ ማዶ ተጉዞ የተለያዩ ቦታ በመሄድ የሙዚቃ ስራዎቹን ማቅረቡ ይታወሳል አሁን በusa( አማሪካ ) የሙዚቃ ስራዎቹን ማቅረቡን እንደ ቀጠለ ነው እሁድ ኦገስት አራት በዲኔቨር የሙዚቃ ስራዎቹን ያቀርባል፡፡
-ፋና ላምሮት አስራ አንደኛ ሳምንት በተለያየ አዲዲስ ጉዳዮች ውድድሩ ይጀምራል ተብሏል ከህዝብ የተመረጠላቸው ሙዚቃዎች ስድስት የተቀሩ ተወዳዳሪዎች ስራዎቻቸውን ከኮከብ ባንድ ጋር ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
– ድምፃዊት ራሄል ጌቱ በባማህር ማዶ ወደ ካናዳ ተጉዛ የሙዚቃ ስራዎችዋን ለማቅረብ እየተዘጋጀች ትገኛለች በፊት የኛዎቹ አባል አሁን እንደእኛ አባል የሆነች ድምፃዊት ራሄል ጌቱ ሁለት አልበም እና የተለያዩ ነጠላ ዜማዎችን ለህዝብ አድርሳለች የመጨረሻ የሙዚቃ ስራዋን የለቀቀችሁ ለጀስቲስያ ፊልም ማጀብያ ”አለች” የተሰኘውን ሙዚቃ ነው፡፡
*በዚህ ሳምንት በሙዚቃዊ ጉዳይ ከተወሩት መካከል፡፡
-የድምፃዊ ዘሩባቤል ሞላ የበኩር አልበም አምስት አመት መድፈኑን በራሱ ማህበራዊ ገፅ አስታውሶናል ብዙ አዳዲስ ጉዳዮች እና በአዳዲስ የሙዚቃ ቅንብር ቀለም የመጣበት ነው “እንፋሎት” አልበም ካውያዬ ፣ ምንድነው ዝምታሽ ፣ ብሶ ፣ ሰባት አርገው ነፍሷን ፣ ሆና እና የመሳሰሉት በውስጡ ይገኛሉ አቀናባሪው ያምሉ ሞላ ነው፡፡
– የድምፃዊ ማስተዋል እያዩ- ”አይከብድም ወይ” እንደ ገና በብዙ መልኩ አሻሽሎት ተጫውቶታል ድምፃዊ ማስተዋል እያዩ በዚህ አመት ”እንዚራ” የተሰኘ አልበም ለህዝብ ማድረሱ አይዘጋም፡፡አሁን ደሞ ”አይከብድም ወይ ” የተሰኘ ሙዚቃ ግጥም ዜማ ዳንኤል ዘውዱ ሲሰራው ቅንብር ሚካኤል መለሰ ሰርተውታል፡፡
– የዚህ ሳምንት የጓደኛ ቀን ተከብሮ እንደ ዋለ ይታወቃል ብዙዎች ድምፃዊያን ስለ ጓደኝነት አቀንቅነዋል በዚህ መልኩ ከወጡ ሙዚቃዎች አንዱ “ጓደኛዬ” የተሰኘ ሙዚቃ ነው በድምፃዊ ቶቦላ አበባው የተቀነቀነ ሲሆን ግጥም ገርዬ በጋሻው ዜማ ድምፃዊ ቶቦላ አበባው ቅንብር ታምሩ አማረ (ቶሚ) ናቸው፡፡ ሙዚቃውን እንድታዳምጡ ጋብዘናችኃል፡፡
* የኔ ቫይብ ሳምንታዊ የአልበም ጥቆማ…
– የድምፃዊ ሳሙኤል ተፈሪ(ሳሞን) ለውጥ የተሰኘ አልበሙ ነው በውስጡ ወደ 15 የሚጠጉ ሙዚቃዎች ሲሆሩ- ወደ አንቺ ስመጣ ፣ትዝታ ፣ ቻው፣ የምኞት አባት ፣ የመጨረሻ ቀን የመሳሰሉት አሉበት፡፡ በግጥም በዜማ በራሱ ሳሙኤል ተፈሪ (ሳሞን ) የተሰራ ሲሆን በቅንብር ቅዱስ ሐብተስላሴ ፣ ኪሩቤል ባጫ ፣ ዳግማዊ ሀብተስላሴ ፣ በድል አብ ብርሀኑ ፣ እዮብ ወርቁ ተሳትፈዋል በማስተሪንጉ ዜማስ ስቱዲዮ ሰርቶታል ፡፡
አዘጋጅ እና አቅራቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ፡፡
Yenevibe.com ገብታችሁ ጎብኙን እናመሰግናለን፡፡