የቴሌቪዥን ኘሮግራም አቅራቢ የሆነውን ትንሳኤ ብርሃን ብራንድ  አምባሳደር ሆነ።ባይሊ የምግብ ማቀነባበሪያ የ…

Reading Time: < 1 minute
የቴሌቪዥን ኘሮግራም አቅራቢ የሆነውን ትንሳኤ ብርሃን ብራንድ  አምባሳደር ሆነ።

ባይሊ የምግብ ማቀነባበሪያ የቴሌቪዥን ኘሮግራም አቅራቢ የሆነውን ትንሳኤ ብርሃን ለቀጣዮቹ 12 ወራት የድርጅቱ የብራንድ አምባሳደር አድርጎ በዛሬው እለት በስካይላይት ሆቴል በተከናወነ መርሐግብር ላይ መሾሙን አሳወቃል።



ከተመሰረተ አራት አመታትን ያስቆጠረው ባይሊ የምግብ ማቀነባበሪያ ለሕጻናት፤ ለወጣቶች እና ለአዋቂዎች ተስማሚ የሆኑ በማር ወለላ የተቀመመ  እና በለውዝ  ጣዕም የሚያመርተው ምርት ለማስተዋወቅ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ኘሮግራም አቅራቢ የሆነውን ትንሳኤ ብርሃን ከሁለት ልጆቹ ጋር  ለቀጣይ አንድ አመት የሚቆይ የብራንድ አምባሳደር ሹመት ፊርማ ስምምነት አድርገዋል።



የባይሊ የምግብ ማቀነባበሪያ ኘሮዳክሽን ማናጀር አቶ ግርማ ተፈራ በፊርማ ስምምነቱ ላይ እንደገለጹት ተቋሙ ከ250 በላይ የሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል የተፈጠረ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ገልጸው  ድርጅቱ በቀጣይ በርካታ አዳዲስ ምርቶችን ወደ ገቢያው ለማቅረብ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።



በፊልም ስራዎቹ እና በቴሌቪዥን ኘሮግራም አቅራቢነቱ የሚታወቀው ትንሳኤ ብርሃን ለቀጣዮቹ 12 ወራቶች ለመስራት ዝግጁ መሆኑን እንዲሁም ባይሊ የምግብ ማቀነባበሪያ መርጦኝ አብሮኝ ለመስራት ስለወሰነ ከልብ አመሰግናለሁ ሲል  ምስጋናውን ለተቋሙ አቅርቧል።

News, Celebrity News, Event Coverage
147210cookie-checkየቴሌቪዥን ኘሮግራም አቅራቢ የሆነውን ትንሳኤ ብርሃን ብራንድ  አምባሳደር ሆነ።ባይሊ የምግብ ማቀነባበሪያ የ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE