“ንስሩ ልጅ” የተሰኘ ፊልም ለእይታ ቀረበ።በሱራፌል መልቲሚዲያ አማካኝነት የተሰናዳው “ንስሩ ልጅ” የተሰኘ …

Reading Time: < 1 minute
*
“ንስሩ ልጅ” የተሰኘ ፊልም ለእይታ ቀረበ።

በሱራፌል መልቲሚዲያ አማካኝነት የተሰናዳው “ንስሩ ልጅ” የተሰኘ አንድ ሰዓት ከሃያ ደቂቃ ርዝማኔ ያለው እና የቤተሰብ ፊልም በዓለም ሲኒማ ለእይታ መቅረብ ጀመረ።

በኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስተሪ ውስጥ የተለያዩ ፊልሞችን በድርሰት ፣ በዳይሬክቲንግ እና በኘሮዲወሲንግ ስራዎች መስክ ከፍተኛ አስተዋጾ እያደረገ በሚገኘው በደራሲና ዳይሬክተር ሱራፌል ኪዳኔ አማካኝነት የተዘጋጀው “ንስሩ ልጅ” ፊልም በትናንትናው እለት በዓለም ሲኒማ በይፋ ተመርቋል።

የፊልሙ ደራሲና ዳይሬክተር ሱራፌል ኪዳኔ በፊልም ምረቃው መርሐግብር ላይ እንገለጸው ስድስት አመት በላይ የወሰደው “ንስሩ ልጅ” ፊልም በብዙ ጥናት ላይ በመመርኮዝ በታዳጊ ልጆች እና ወላጆቻቸው ላይ ትኩረት በማደረግ ልጅን ከወላጅ ጋር በማቀራረብ መልካም ትውልድን ለመፈጠር እየተሰራ ባለው ስራ ላይ ተጨማሪ ግብአት እንዲሆን በማሰብ መዘጋጀቱን ገልጿል።

“ንስሩ ልጅ” ፊልም ለተከታዮቹ አራት ሳምንት ዘወትር እሁድ ከረፋዱ 5:00 ሰዓት ጀምሮ በአለም ሲኒማ እና በቀጣይ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች እና በተለያዩ ሲኒማ ቤቶች ለእይታ የሚቀርብ ሲሆን ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር እንዲመለከቱት ደራሲ መልዕክት አስተላልፏል።
147170cookie-check“ንስሩ ልጅ” የተሰኘ ፊልም ለእይታ ቀረበ።በሱራፌል መልቲሚዲያ አማካኝነት የተሰናዳው “ንስሩ ልጅ” የተሰኘ …

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE