ከንቲባ ከድር ጁሀር በቁልቢ ገብርኤል አመታዊ የንግስ በዓል ላይ ለመታደም ድሬዳዋ የመጡ እንግዶችን የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበልና ወደ በዓሉ ስፍራም ለሚጓዙትም ሽኝት አደረጉ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርና የበዓሉ የፀጥታ ግብረ ኃይል አባላት እንግዶቹን ገነት መናፈሻ ተብሎ በሚጠራው የከተማው መግቢያ ሥፍራ ላይ ተገኝተው የመጠጥ ውሃ በመስጠት ነው አቀባበል ያደረጉላቸው።
በዓመት 2 ጊዜ የሚከበረውን የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር ለማክበር በታቀደው መሰረት በዓሉ በሰላም እንዲከበር አስፈላጊው የፀጥታ ዝግጅት መደረጉን የአስተዳደሩና የምስራቅ ኢትዮጵያ የጸጥታ ግብረኃይል መግለጹ ይታወሳል።
በዚህም መሰረት ለበዓሉ ወደ ድሬዳዋ የገቡ እንግዶች በሰላም ገብተው ወደ በዓሉ ስፍራ በሰላም እየተሸኙ ነው።
በወጭ አና ገቢ ተሽከርካሪዎችም ላይ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይኖር በመንገድ ትራፊክ በኩል ትኩረት ተሰቶ መጨናነቆች አና አደጋዎች እንዳይከሰቱ የትራፊክ ደንብ አስከባሪ አባላት እየሰሩ ይገኛሉ።
ለክብረ በዓሉ የሚጓዙት እንግዶች እንደተናገሩት በድሬዳዋ ከተማ በተደረገላቸው አቀባበል እና ማረፊያ ስፍራ ተዘጋጅቶላቸው በነበራቸው ቆይታ መደሰታቸውን ገልፀው በተለይም ለድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ያላቸውን ልባዊ ምስጋና ገልጸዋል።
ድሬዳዋ ኮምኒኬሽን