አቢሲኒያ የኢንዲስትሪ ሽልማት የፊታችን እሁድ ይካሄዳል።
የአቢሲኒያ ሽልማት እህት ኩባንያ የሆነው አቢሲኒያ የኢንደስትሪ ሽልማት ድርጅት በየዓመቱ የሚሸልመውን የኢንደስትሪ ሽልማት የፊታችን ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል እንደሚያካሄድ አሳወቀ።
የአቢሲኒያ ሽልማት ድርጅት መሥራችና ፕሬዚዳንት አቶ ግርማ በቀለ የሽልማቱን ዝግጅት አስመልክተው በዛሬው እለት ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እንደገለጹት አቢሲኒያ የከፍተኛ ክብር ሽልማት ፣ አቢሲኒያ የኢንዱስትሪ ሽልማት እና ወርልድ ከላስ የጥራት ሽልማት ድርጅት የጎሊደን ዌይ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እህትማማች ድርጅቶች ሲሆኑ በመደበኛ ሽልማትም ሆነ በጥራት ሽልማት የድርጅቱ ዋና አላማ ትጉኃንን በመሸለም የምርትና አገልግሎት ጥራት እንዲሻሻል የበኩሉን አስተዋፅአ በማድረግ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ባሳለፍነው ሐምሌ 14 እና የፊታችን ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም የ2ኛውን የኢንዱስትሪ ሽልማት ፣ ነሐሴ 19 ቀን የ2016 ዓ.ም በ17ኛው መደበኛ ሽልማት የአመቱን ሎሬቶች ሽልማት እንዲሁም ከፍተኛ ክብር የሎሬቶች ሽልማት ደግሞ ነሐሴ 26 ቀን የቀድሞ ሎሬቶች የሽልማት ደረጃ ማስተካከያና በልዩ ድምቀት የማህበረሰብ መተዋወቂያና ማጽኛ ሽልማት እንደሚከናወን አቶ ግርማ በቀለ ጨምረው ገልጸዋል።
የላቀ ስራ ለሰሩ እና ዘመናዊ አሰራርን ለሚከተሉ ተቋማት መሸለም ጥራትን ያለውን ምርት እና አገልግሎትን ለማግኘት
ለማኅበረሰብ የሚያቀርቡ ሙያተኞችን እና ተቋማትን በመፍጠር ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ስልጣኔ እና እድገት እንዲመጣ ማድረግን ራዕዩ አድርጎ የተመሠረተው አቢሲኒያ የጥራት ሽልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ሽልማት ሁሉንም የኢንዱስትሪ ክፍሎች የያዘ ሲሆን የሰራተኛው ክፍል ፣ የስራ መሪዎች ፣የግልና የመንግስት ተቋማትን ሸልሟል።