በብድር የኤሌክትሪክ መኪና መመቻቸቱ ተገለጸ።ከበላይነህ ክንዴ የመኪና መገጣጠሚያ ጋር በጥምረት የሚሰራው ጎሸ…

Reading Time: < 1 minute
*
በብድር የኤሌክትሪክ መኪና መመቻቸቱ ተገለጸ።

ከበላይነህ ክንዴ የመኪና መገጣጠሚያ ጋር በጥምረት የሚሰራው ጎሸር ትሬዲንግ ፤ ከማህደር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኀብረት ስራ ማኅበር አማካኝነት 25 በመቶ ለቆጠቡ መኪና ፈላጊዎች በዛሬው እለት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኘው አዳራሽ በተከናወነ ልዩ መርሐግብር የመጀመሪያ ዙር የኤሌክትሪክ መኪናዎችን አስረከቡ።

ማህደር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኀብረት ስራ ማኅበር ዋና ስራ አስኪያጅ መላከሰላም ፍስሀ አረጌ ሁለት አመት ከስድስት ወር ውስጥ ከ1600 በላይ አባላት ያፈራ ሲሆን 85.3 ሚሊዮን ብር ለአባላቱ በጥሬ ገንዘብ እና በቁሳቁስ ማበደሩን ገልጸዋል።

በተመሠረተ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለውጥን እያሳየ የሚገኘው ከማህደር የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ የኀብረት ስራ ማኅበር በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተለያየ አካበቢ ሶስት ቅርንጫፎችን በመክፈት ዜጎች ህይወታቸው እንዲለወጥ ጠንክሮ በመስራት ላይ እንደሚገኝ መላከሰላም ፍስሀ አረጌ ገልጸው በማኀበራዊ ተሳትፎ በኩል በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ መኪናዎን እያቀረበ የሚገኘው ከበላይነህ ክንዴ የመኪና መገጣጠሚያ ጋር በጥምረት የሚሰራው ጎሸር ትሬዲንግ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ደረጀ መኮነን መኪኖቻችን በኤሌክትሪክ ቻርጅ መሥራታቸው ለሀገር ብዙ ጥቅምን ያስገኛሉ ያሉ ሲሆን አሁን ላይ አለም የደረሰበት የመጨረሻ ቴክኖሎጂ የተገጠመላቸውን ተሽከርካሪዎችን ለተጠቃሚዎች በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

አቶ ደረጀ መኮነን ጨምረው እንደገለጹት ዋጋውም ከመኪናው ውበት እና ከሚሠጠው ጠቀሜታ አንጻር ሲወዳደር ተገቢ ዋጋ ነው የወጣለት ብለዋል።
146670cookie-checkበብድር የኤሌክትሪክ መኪና መመቻቸቱ ተገለጸ።ከበላይነህ ክንዴ የመኪና መገጣጠሚያ ጋር በጥምረት የሚሰራው ጎሸ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE