“የምትተከል ሀገር የሚያፀና ትውልድ”
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ “የምትተከል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ የ2016 ዓ.ም የአረንጋዴ አሻራ ከ2ሺህ በላይ የሚሆኑ የቢሮ ሰራተኞችን እና አጋር ተቋማትን በማስተባበር ሀገር በቀል ችግኞች የመትከል መርሀ-ግብር በእንጦጦ ፓርክ ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይንሸት ዘሪሁን የችግኝ ተከላውን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ዛሬ የተተከሉትን ችግኞች ከመትከል ባሻገር ፀድቀው ዛፍ እስኪሆኑ ድረስ በመኮትኮት በመንከባከብ እንዲሁም የነገ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ሕፃናትም ሁለንትናዊ እድገታቸው እንዲረጋገጥ መስራት ይገባል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞች ሲተክል የቆየ ሲሆን በዚህ ዓመትም ከ20 ሺህ በላይ ችግኞች ለመትከል በታቀደው መሰረት ከ14ሺህ በላይ በዛሬው ዕለት በዚሁ በእንጦጦ ፓርክ የተተከለ ሲሆን ከ6 ሺህ በላይ አድገው ለምግብነት የሚውሉ የተለያዩ ችግኞች በ6ቱ የቢሮው የክብካቤ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ላይ ይተከላሉ ተብሏል።