የመምህር ሥዩም ጉልላት ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጸመ።
በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ ምክትል አዘጋጅና በተለያዩ አህጉረ ስብከት ሰባኬ ወንጌል በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት መምህር ሥዩም ጉልላት ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ዛሬ ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም ተፈጸመ።
መምህር ሥዩም ጉልላት ሐምሌ 7 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በደረሰባቸው ድንገተኛ የመኪና አደጋ ምክንያት ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።
መምህር ሥዩም ጉልላት በ1978 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ቀጸባ ማርያም በተባለ ሥፍራ የተወለዱ ሲሆን ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ በደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም፣ በጅማ አበልቲ ኪዳነ ምሕረት ገዳም፣ ሰዋስዎ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ በቅድስት ሥላሴ ዪኑቨርሲቲ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እና በተለያዩ ማሰልጠኛ ተቋማት ትምህርታቸውን መከታተላቸው የሕይወት ታሪካቸው ያስረዳል።
Via ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ