በ4 ቢሊዮን ብር የቅዱስ ያሬድ ሙዚየም ሊገነባ ነውቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ምዕራፍ፣ ዝማሬና መዋሥዕት …

Reading Time: < 1 minute
*
በ4 ቢሊዮን ብር የቅዱስ ያሬድ ሙዚየም ሊገነባ ነው

ቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ምዕራፍ፣ ዝማሬና መዋሥዕት የተሰኙትን 5 የዜማ መጻሕፍት የደረሱ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ናቸው፡፡ ብቸኛው የግእዝ ሥነ ጽሑፍ መስራች እንደሆኑም ይነገራል፡፡ ለእኚህ ኢትዮጵያዊ ሊቅ የሕይወት ታሪካቸውን የሚዘክር ሙዚየም በታላቁ ራስ ዳሽን ተራራ ላይ በ4 ቢሊዮን ብር ወጪ ሊገነባ ነው፡፡

የፕሮጅክቱ ሰብሳቢ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ ቅዱስ ያሬድ የመጀመርያው የዜማ ሊቅ ብቻ ሳይሆን በድርሰትም የመጀመርያው መሆናቸውን ገልጾ በስማቸው የሚገነባው ሙዚየም የቅኔ ትምህርት፣ የዝማሬ ትምህርትና በርካታ ዘርፎችን የሚያካትት እንዲሁም ብዙ ሊቃውንትን የሚያፈራ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ጋዜጠኛው አክሎም የአካባቢው ገበሬ ፕሮጀክቱን ስለወደደው 6 ሄክታር መሬት መስጠቱን ገልጿል፡፡ በዚህ ሙዚየምም የአሁኑ ትውልድ የራሱን አሻራ የሚያሳርፍበት ታሪካዊ፣ ሀይማኖታዊ እና ሀገራዊ ፋይዳ እዳለውም ጨምሯል፡፡ እነቅዱስ ላሊበላ በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የሰሩት አስከዛሬ ላለው ትውልድ እንደጠቀመ ሁሉ እኛም ይሄንን በመስራት ለቀጣይ ትውልድ ትልቅ መሰረት የምንጥልበት ነውም ብሏል፡፡

በታላቁ ራስ ዳሽን ተራራ በደብረ ሐዊ ገዳም አቅራቢያ በሚገነባው ሙዚየም ውስጥ አንዱ የሆነው ህንፃ ቤተክርስቲያን የኖህ መርከብን ቅርጽ የሚይዝ መሆኑንም የፕሮጀክቱ ዋና አርክቴክት መኮንን ወርቁ ተናግረዋል፡። የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ይዘትም አካባቢውን የዋጀ እና በዋሻ መልክ የሚገነባ ሲሆን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ታግዞ የሚከወንም መሆኑንም አርክቴክቱ አንስተዋል፡፡

ሙዚየሙ በስማቸው የሚገነባላቸው ሊቁ ባለቅኔ የዜማ አባት ቅዱስ ያሬድ መጻሕፍትን በጣዕመ ዜማ ደርሰዋል፡፡
146210cookie-checkበ4 ቢሊዮን ብር የቅዱስ ያሬድ ሙዚየም ሊገነባ ነውቅዱስ ያሬድ ድጓ፣ ጾመ ድጓ፣ ምዕራፍ፣ ዝማሬና መዋሥዕት …

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE