«ዘመን ተዋህዶ ኤክስፖ» በኤግዚብሽን ማዕከል
ማርኮናል ኦርጋናይዘር ፣ ከሎዛ ኦርቶድክሳዊ ኹነቶች አዘጋጅ እና ከመንፈሳዊ ቲክቶከሮች ጋር በጋራ በመሆን ያሰናዳት የመጀመሪያው «ዘመን ተዋህዶ ኤክስፖ» በአዲስ አበባ ኤግዚብሽን ማዕከል ከሐምሌ 12 እስከ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ዛሬ ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓ.ም በጁፒተር ሆቴል በሰጡት የጋራ መግለጫ አስታወቁ።
መጪውን አዲስ አመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ‹‹ዘመን ተዋሕዶ ኤክስፖ›› በሚል መጠሪያ በተጨማሪም ‹‹ለጋራ እድገት በአብሮነት›› በሚል መሪ ቃል ለተከታታይ 10 ቀናት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ዛሬ ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓ.ም በጁፒተር ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል።
ይህ የተዋሕዶ ኤክስፖ ፕሮጀክት ከተለመደው የኤግዚቢሽን እና ባዛር አቀራረብ ለየት ባለ መልኩ በልዩ አውደ ምህረት ቅኝት እና ሁሉን አካታችን በሆነ መዋቅር እጅግ አነስተኛ በሆነ የመገቢያ ዋጋ በማቅረብ ከአልኮል መጠጥ እና ከሀይማኖታዊ ስርዓቱ ውጪ ከሆኑ ምርቶች ውጪ ያሉ የትኛውም የቤተ ክርስቲያን እና የማህበረሰብ መገልገያ ቁሳቁሶችን በማካተት የህብረተሰቡን አቅም ያማከሉ ምርት እና አገልገሎቶችን በማቅረብ በዘላቂነት በመስራት የህብረተሰቡ የኑሮ ገብአቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ የሚገኝበት የገበያ አማራጭ የማድረግ አላማ ያለው እንደሆነ አዘጋጆቹ ተናግሯል።
ዘመን ተዋሕዶ ኤክስፖ ላይ በቀን ከ5ሺህ ህዝብ በላይ እንደሚጎበኘው የሚጠበቅ ሲሆን ከ150 በላይ ነጋዴዎች እንደሚሳተፉም ተነግሯል።
የመግቢያ ዋጋ 50 ብር እንደሆነ በተገለጸው ኤክስፖ ላይ 10 ታላላቅ ጉባኤዎች በማታው መርሃ ግብር የተዘጋጀ ሲሆን በቂ የመኪና ማቆሚያ እና ልዩ የህጻናት ማቆያ እንደተዘጋጀ ተገልጿል።