በሞቀው ውድድር ዳኞች ጠንክረው እያንዳንዷን ነገሮች በጥንቃቄ እንጓዙ አስተያየት ሰተዋል፡፡https://tel…

Reading Time: 2 minutes
በሞቀው ውድድር ዳኞች ጠንክረው እያንዳንዷን ነገሮች በጥንቃቄ እንጓዙ አስተያየት ሰተዋል፡፡



ፋና ላምሮት አስራ ሰባተኛ ምዕራፍ ዘጠነኛ ሳምንት ሁለቱም ምድብ የተወጣጡ ስምንት ተወዳዳሪዎች ከኮከብ ባንድ ጋር ውድድራቸውን አድርገዋል፡፡

* ምን አዲስ ነገር አለ

– ተወዳዳሪዎች በመድረኩ ያልተለመዱ ሙዚቃዎች የዚህን ዘመን እና የዚህያን ዘመን ሙዚቃ አቅርበዋል፡፡ለምሳሌ ቴዎድሮስ ካሳሁን( ፅጌሬዳ) ፣ ማስተዋል እያዩ( እቴ) ፣ ዳዊት መለሰ( ፍረጂኝ) ፣ ተፈራ ነጋሽ (ትዝታ ፍቆቷ) ይጠቀሳሉ ፡፡

-በየኔ ቫይብ የዚህ ሳምንት ካስገረሙን ተወዳዳሪዎች በሁለተኛ ሳምንት ሌላ አስር ሺህ ነጥብ የተመዘገበበት ነበር ፡፡ ለተወዳዳሪ ጴጥሮስ ማስረሻ በአካል ሳይፈተን የተሰኘውን የጥላሁን ገሰሰ ሙዚቃ ሲጫወት ዳኞች ተደስተው ሙሉ ነጥብ ሰተውታል፡፡በሌው ናሆም ነጋሽ ( ቴዎድሮስ ካሳሁን( ቴዲ አፍሮ) ፅጌሬዳ በምርጥ አዘፋፈን ስያስደምመን ተመልክተናል፡፡

-በርከት ያሉ ተመልካቾች የተወዳዳሪ ቤተሰቦች የሙዚቃ አድናቂዎች ወደ ፊት ለመወዳደር እያጤኑ ያሉ መጪ ተወዳዳሪዎች ስቱዲዮ ድረስ በመገኘት ውድድሩን ተከታትለዋል ለተወዳዳሪዎች ትልቅ አቅምም ሲሆኑ ታይተዋል፡፡

-በዚህ ዙር በሁለት ጎራ ተከፍለው ሲወዳደሩ የነበሩ ተወዳዳሪዎች በአንድ ሆነው ውድድራቸውን ጀምረዋል ፡፡በተጨማሪም በዘጠነኛው ሳምንት አጠቃላይ 16 ሙዚቃ ሲጫወቱ አብዛኛው የንዋይ ደበበ ፣ የጥላሁን ገሰሰ እና የማዲንጎ አፈወርቅ ሁለት ሁለት ስራ ቀርበዋል፡፡

– በመድረኩም ከተሰሩ ሙዚቃዎች ግጥም ዜማ እንዲሁም በቅንብሩ የሰሩት አበጋዝ ክብረወርቅ ፣ሚካኤል ሀይሉ/ሚኪ ጃኞ/ ፣ ቴዲ ማክ ( አይቤክስ ባንድ)  ፣ ኤክስብረስ ባንድ እና የመሳሰሉት …በግጥም ዜማ ሻለቃ ክፍሌ አቦቸር ፣ አበበ ብርሀኔ ፣ የሸዋ ልዑል መንግስቱ ፣ ፀጋዬ ደቦጭ ፣ ቴዲ አፍሮ ፣ አበበ መለሰ ፣ ይልማ ገብረዓብ ፣ ንዋይ ደበበ የመሳሰሉትን ስራ የሰሩትን በመድረኩ ቀርቧል፡፡

-አስራ ስምንተኛው ምዕራፍ  የድምፃዊያን የባለ ተስዖጦ ውድድር ምዝገባ ተጀምሯል 8333 በመደወል እና ፋና ብሮድካቲንግ ኮርፖሬት ጊቢ በመገኘት ለቀጣይ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፡

*ዳኞች ከስልትም ከስሜትም አስተያየት ሰተዋል፡፡

የዘፈን ምርጫ ፣ (ኪ) አዘፋፈን ምጠና መስማማት መረጣ ፣ ግጥም መጥፍት ችግር እርምት እንዲኖረው ፣ የዜማ ከርቭ ፣ ዘፍኖ ማሳመን ብቃት ፣ ቫልዩ አድ ( በነበረው ላይ አዲስ ነገር መጨመር) ፣ ቅኝት ፣ ሪትም ፣ ለውጥ/ ምክርን ተግባራዊ ማድረግ ፣ ኤክስፕሬሽን ( አገላለፅ ) ፣ ዳይናሚክስ ፣ ብልሀትነት ፣ የማይክ አጠቃቀም ፣ በራስ መንገድ ማዜም ፣ በራስ ድምፅ መዝፈን ፣ ቫራይቲ( የሙዚቃ ምርጫ ማስፋት) ፣ ውበት የድምፅ ፣ የዜማ እጥፍት ፣ መቀለፅ ፣ በጥንቃቄ መጓዝ እና የመሳሰሉት በመድረኩ ቀርቧል፡፡

*ኮከብ ባንድ በብቃት ከ ተወዳዳሪዎች ጋር ሆነው 16 ሙዚቃዎችን ተጫውተዋል፡፡

– (ጥላሁን ገሰሰ/ ስንት አየሁ  ) ፣ (ማስተዋል እያዩ ( እቴ)፣(መሀሙድ አህመድ/ ፍቅር አዛዥ ነው ወይ) ፣(ቴዎድሮስ ታደሰ/ በፍቅርሽ)፣(ሙሉቀን መለሰ/ ፍቅሯ ቀለለ ስል)  ፣ (ቴዎድሮስ ታደሰ / እቴ በገላሽ )፣ (ዳዊት መለሰ/ ፍረጂኝ)፣ (ጥላሁን ገሰሰ/ አካም ነጉማ) ፣(ነዋይ ደበበ/ በበረሃው አውሎ ንፋስ )፣(ነዋይ ደበበ / ያምራል ጥለትሽ ) ፣(ዳዊት ፅጌ / እትቱ) ፣(ቴዲ አፍሮ/ ፅጌሬዳ  )፣(ማዲንጎ አፈወርቅ / ጎዳናው  ) ፣(ተፈራ ነጋሽ/ ትዝታ ናፍቆቷ )፣(አለማየሁ እሸቴ ፣ ህይወቴ  አባቴ ነው  ፣(ማዲንጎ አፈወርቅ/ ስያሜ አጣሁላት)
 
* ዳኞች ለተወዳዳሪዎች ስንቅ ለሕይወታችን ብርታት የሚሆን ሰተውናል፡፡

* ብሩክ አሰፋ፡ ቅኝትን ለማሻሻል እራሳችሁን አዳምጡ፡፡

የሹምነሽ ታዬ:- ሙዚቃ ይዛችሁ ስትመጡ የትኛውን ችሎታ ላሳይበት ብላችሁ አስቡበት፡

አማኑኤል ይልማ:- አንድ አንድ ሙዚቃዎች ስትጫወቱ ካልተስማማችሁ አታንሱት፡፡

* ያለፉ ተወዳዳሪዎች እንዲሁም ተሰናባቹን እንጠቁም፡፡

ጴጥሮስ ማስረሻ- 60375 አጠቃላይ በማምጣት፡፡
-ናሆም ነጋሽ- 59758 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ሱራፌል ደረጄ-59404 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
– አብርሀም ማርልኝ-59404 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
– ሄኖክ አለሙ – 59102 አጠላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ኤርሚያስ ዳኛው-58936 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ጌታሁን ተረፈ-58905 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት ወደ ቀጣዩ ፍልሚ ተቀላቅለዋል፡፡፡፡

…የእለቱ ተሰናባች ዘላለም ፀጋዬ– 58751 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት… እጅግ አስገራሚ ድምፃዊ ነበር፡፡  የሙዚቃ ምርጫውን ሁሌ እያጠናከረ የሚጓዝ የድምፃዊ ቀመር ዩሱፍን ፣ አሊ ቢራ ፣ የፀሐዬ ዮሐንስን ሙዚቃ አሞላቆ ይጫወታል ዳኞችም መስክረውለታል፡፡ በእለታዊ የሙዚቃ አቀራረብ ሊሰናበት ችሎሏል፡፡

* ዘላለም ፀጋዬ ” ታላቅ እህቴን ፣ ዳኞችን ፣ ተወዳዳሪዎችን ፣ ኮከብ ባንድን ፣ ሁሉንም እግዜር ያክብርልኝ” ሲል ገልጿል፡፡ ፋናም አብሮነቱን ገልፆ ከ10000 ብር ጋር ሸኝቶታል፡፡

አዘጋጅ አቅራቢ እና ዘጋቢ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ፡፡
ፋና ላምሮት
በቸር ያገናኘን Yenevibe.com ጎብኙን
146110cookie-checkበሞቀው ውድድር ዳኞች ጠንክረው እያንዳንዷን ነገሮች በጥንቃቄ እንጓዙ አስተያየት ሰተዋል፡፡https://tel…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE