አሐዱ ባንክ ከ175 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ ማስመዝገቡን ገለጸ።
አሐዱ ባንክ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በሁሉም መስክ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን እና የተለያዩ ምንጮችን ተጠቅሞ ገቢውን 1.15 ቢሊዮን ብር በማድረስ ከታክስ በፊት ከ175 ሚሊዮን ብር በላይ ማትረፉን አስታወቀ።
በተጨማሪም ባንኩ የተከፈለ ካፒታሉን 1.03 ቢሊዮን ብር በላይ ያደረሰ ሲሆን፤ ይህም የባንኩን የፋይናንስ አቅም የሚያጎለብት እና ባንኩን ለቀጣይ ማስፋፊያዎች እና ኢንቨስትመንቶች መልካም ዕድልን የሚፈጥር ይሆናል፡፡
አሐዱ ባንክ “ከብዙዎች ለብዙዎች” በሚልው መርሁ አገልግሎቱን በመላው ሀገሪቱ ለማዳረስ በነደፈው እቅድ መሰረት የቅርንጫፎቹን ብዛት 104 አድርሶ ምቹ እና ፈጣን አገልግሎቶችን በመስጠት ከ 700 ሺህ በላይ ደንበኞችን ማፍራት ችሏል፡፡
በተመሣሣይ ባንኩ ጠቅላላ ሃብቱን 6.3 ቢሊዮን ብር በማድረስ የተስተካከለ የተቀማጭ/ተከፋይ ገንዘብ ሚዛን ፣ ጠንቃቃ የሃብት አጠቃቀም እና አዋጭ የመዋዕለ ንዋይ አስተዳደር የመተግበር አቅሙን አስመስክሮኣል፡፡
የባንኩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰፊዓለም ሊበን እንደገለጹት አሐዱ ባንክ አቅዶ የተነሳበትን ብዙዎችን የሚያካትት የፋይናንስ ተጠቃሚነትን፣ ጠንካራ ቤተሰባዊነትን፣ በትብብር መሥራትን እንዲሁም ዘመኑ የደረሰበትን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ በማድረጉ በደንበኞቹ ዘንድ ዕምነትንና ላቅ ያለ ተቀባይነትን በማግኘታችን ከ 4.6 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ መሰብሰብ ችለናል ብለዋል፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው አያይዘው በተለይም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአስቸጋሪ የቢዝነስ አውድ ውስጥ ብናሳልፍም ልዩ ልዩ የፋይናንስ አገልግሎቶችን በማቅረብ፣ ላቅ ባለ የደንበኛ አያያዝ እና አገልግሎት አሰጣጥ ይህንን ውጤት ልናስመዘግብ ችለናል ብለዋል፡፡