በኢትዮጵያ የመጀመሪያዎቹ 40 የማሳጅ ህክምና ባለሞያ ተማሪዎች ተመረቁ!
ዌልነስ ሜዲካል ኮሌጅ በዘለማድ የሚሰራውን የማሳጅ አገልግሎት የሚያስቀርና በሳይንሳዊ ዘዴ ህክምናው የደረሰበትን የልህቀት ደረጃ በጠበቀ መልኩ ተማሪዎችን አሰልጥኖ ትናንት ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓም አስመርቋል።
ዌልነስ ሜዲካል ኮሌጅ በተለይም በዘልማድ የሚሰራውን የማሳጅ አገልግሎት የሚያስቀርና በሳይንሳዊ ዘዴ ህክምናው የደረሰበትን የልህቀት ደረጃ በጠበቀ መልኩ 40 በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ ዛሬ አስመርቋል።
የተቋሙ መስራች ዶክተር ሰላም አክሊሉ “ኢትዮጵያ ጨዋነቷን አስጠብቃ እንድትቀጥል ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። በማሳጅ ስም በቂ እውቀት የሌላቸው ሰዎች የሰውን ገላ እንዲነኩ መፍቀድ የለብንም፤ ይልቁን የአጥንት፤ የነርቭ፤ የጡንቻና ደምስር አቀማመጥ በህክምና በተጠና መልኩ ታውቆ ማሳጅ መሰጠት አለበት። ትምህርት ቤታችን ይህንን ያማከለ ትምህርት በከፍተኛ ባለሙያዎች እየሰጠ ይገኛል።” ብለዋል።
የአሻራ ዌልነስ ሰፓ ባለቤትና የህይወት ክህሎት አሰልጣኝ አቶ ያሬድ አለማየሁ “ያለእውቀት የተገባ የማሳጅ አገልግሎት ወደሴተኛ አዳሪነት ያስገባል የለመዱት ለመማር ፍቃደኛ ባይሆኑ እንኳ አሁንም በር አለ ልንላቸው ይገባል።” ብለዋል።
የማሳጅ ህክምና ትምህርት ለመጀመሪያ ጊዜ በአገራችን እንዲሰጥ አስተዋፅኦ ካደረጉት መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ዮሴፍ በቀለ በበኩላቸው አሁንም ቢሆን ሀላፊነቱን መውሰድ የሚገባው መንግሥት ብቻ ነው።
ፍቃድ ሰጪው አካል ፍቃዱን ከመስጠቱ በፊት የሚጠይቃቸው መስፈርቶች በስራ ላይ መዋላቸውን እና ትክክለኛ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን መከታተል አለበት። ህግን ተከትለው እንዲሰሩ ማድረግ ይገባዋል ብለዋል።
ዶ/ር ሰላም ከ37 አመት በላይ በውጪም ሆነ በአገር ውስጥ ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ ባለሞያ ናቸው።