ደም ልጋሾችን እናመሠግናለን !ኤግል ቪው ሚዲያ ኤንድ ኮንሰልታንሲ ከኢትዮጵያ ደም እና ህበረ ህዋስ ባንክ አ…

Reading Time: < 1 minute
*
ደም ልጋሾችን እናመሠግናለን !

ኤግል ቪው ሚዲያ ኤንድ ኮንሰልታንሲ ከኢትዮጵያ ደም እና ህበረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ጋር በመተባበር በርካታ ለጋሾች ደም ልገሳ እንዲከናወን የማድረግ ሰራዎችን በዛሬ ዕለት አከናወነ፡፡

በልገሳ ፕሮግራም ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የማዕድን ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ መሃመድ ራፊዕ አባራያ ደም መለገስ ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ህይወትን መታደግ በመሆኑ የህሊና እርካታ የሚሰጥ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ደምና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አሸናፊ ታዘበው (ዶ/ር) በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንደተናገሩት በአሁኑ ወቅት እንደ ሀገር ያለውን የደም እና የደም ተዋጽዎ አቅርቦትን ለማሳደግ ኤግል ቪው ሚዲያ ኤንድ ኮንሰልታንሲ የተለያዩ አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር ያከናወነው ተግባር እጅግ የሚያስመሰግን መሆኑን ጠቅሰው ለተደረገው ተግባር ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የኤግል ቪው ሚዲያ ኤንድ ኮንሰልታንሲ ስራ አስኪያጅ አቶ ያለው ጌታቸው በበኩላቸው ይህንን በጎ ተግባር ድርጅታቸው ኤግል ቪው ሚዲያ ኤንድ ኮንሰልታንሲ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣ በማሰብ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ያከናወነው የደም ልገሳ ማስተባበር ፕሮግራም ቀጣይነት እንደሚኖረው ገልጸዋል።

በልገሳው የማዕድን ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት እና የማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት አመራሮችና ሠራተኞች፣ የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ የስራና ክሎት ሚኒስቴር ሠራተኞች እና የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ተመራቂ ተማሪዎች ተሳትፈዋል፡፡ የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ከሰኔ 26 እስከ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል ይሆናል፡፡
143960cookie-checkደም ልጋሾችን እናመሠግናለን !ኤግል ቪው ሚዲያ ኤንድ ኮንሰልታንሲ ከኢትዮጵያ ደም እና ህበረ ህዋስ ባንክ አ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።
ጌች ሐበሻ

ጌች ሐበሻ

ጌትነት ተመስገን (ጌች ሐበሻ) በማኀበራዊ ጉዳዮች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በተለያዩ የማኀበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመጻፍ ንቁ ተሳታፊ ነው።

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE