በሀገራችን የመጀመሪያዉ የሚዲያ አዋርድ ነሐሴ ወር ላይ ይደረጋል ተባለ https://telegra.ph/file…

Reading Time: < 1 minute
በሀገራችን የመጀመሪያዉ የሚዲያ አዋርድ ነሐሴ ወር ላይ ይደረጋል ተባለ



ቴሌቪዥን ፣ ሬዲዮ እና ጋዜጦች ላይ የሚሰሩ የሚዲያ ባለሞያዎችን (ጋዜጠኞችን) የሚሽልመዉ ይህ አዋርድ በመጀመሪያ ዓመቱ በ18 ዘርፎች ዉድድሩን እንደሚያደርግ ተነግሯል።



የአዋርዱ አዘጋጆች ከባለፈዉ ዓመት ሰኔ ወር ጀምሮ የተላለፉ ፕሮግራሞች እና ለሰባት ወራት በስራ ላይ የነበሩ የሚዲያ ባለሞያዎች ብቻ በእጩነት እንደቀረቡ ያነሱ ሲሆን በአዋርዱ ላይ የቀረቡት ሁሉም እጩዎች መስፈርቶችን ያሟሉት ብቻ ናቸዉ ተብሏል። ሆኖም በመረጃዎች ክፍተት ያልተካተቱ ፕሮግራሞችና ጋዜጠኞች ካሉ የመገናኛ ብዙሃኑ በሚቀጥሉት አምስት ቀናት ዉስጥ ማሳወቅ ይችላሉም ተብሏል።



አሸናፊዎች በዳኞች እና በህዝብ ድምፅ የሚመረጡ ሲሆን ህዝቡ በመጀመሪያ ዙር በኦን ላይ ethio-mediaaward.com በመግባት ድምፅ መስጠት ይችላል የመጨረሻዎቹ እጩዎች ሲታወቁ ደግሞ ከኦን ላይ በተጨማሪ ተወዳዳሪዎች በሚወከሉበት ኮድ በኤስ ኤም ኤስ (sms) ድምድ ይሰጣሉ።



በሚዲያ አዋርዱ ላይ ከተካተቱ ዘርፎች አንዱ በህዝብ ድምፅ ብቻ የሚመረጠዉ የዓመቱ ምርጥ ጋዜጠኛ ሲሆን የዚህ ዘርፍ ተወዳዳሪዎች የሚለዩት ህዝቡ በሚልካቸዉ እጩዎች እንደሆነ ተነግሯል ፣ ለዚህም በሚቀጥሉት 10 ቀናት በ0933232373 በፁህፍ መልህክት ብቻ አሁን ላይ በሚዲያ ስራ ላይ የሚገኙ ምርጥ የሚሏቸዉን ጋዜጠኞች እጩ አድርገዉ ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።

ከ40 ዓመታት በላይ በጋዜጠኝነት ሞያ የቆየችዉ የሸገር የጨዋታ ፕሮግራም አቅራቢዋ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ የመጀመሪያዉ ‘የሚዲያ አዋርድ’ የህይወት ዘመን ተሸላሚ እንደምትሆንም በጋዜጣዊ መግለጫዉ ላይ ተረጋግጧል።

የህሕይወት ዘመን ተሸላሚ ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ገብረ ወልድ መሆንዋንም ተገልጿል፡፡

የመጀመሪያዉ የሽልማት ፕሮግራም ዘርፎች

1.  የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን የመዝናኛ ፕሮግራም
2.  የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ የመዝናኛ ፕሮግራም
3.  የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን የመዝናኛ ፕሮግራም ወንድ አቅራቢ
4.  የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን የመዝናኛ ፕሮግራም ሴት አቅራቢ
5.  የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ወንድ ዜና አንባቢ
6.  የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ሴት ዜና አንባቢ
7.  የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ ሴት ዜና አንባቢ
8.  የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ ወንድ ዜና አንባቢ
9.  የዓመቱ ምርጥ የስፖርት ፕሮግራም
10.  የዓመቱ የህዝብ ምርጫ/ምርጥ ጋዜጠኛ
11.  የዓመቱ ምርጥ አይደል ሾዉ
12.  የዓመቱ ምርጥ ዶክመንተሪ
13.  የዓመቱ ምርጥ የዜነ ዘገባ
14.  የዓመቱ ምርጥ አርቲክል/ፕሪንት ሚዲያ
15.  የዓመቱ ምርጥ ዲጄ
16.  የዓመቱ ምርጥ የቴሌቪዥን ጣቢያ
17.  የዓመቱ ምርጥ የሬዲዮ ጣቢያ
18.  የዓመቱ ምርጥ ጋዜጣ
የዓመቱ የህይወት ዘመን ተሸላሚ
142070cookie-checkበሀገራችን የመጀመሪያዉ የሚዲያ አዋርድ ነሐሴ ወር ላይ ይደረጋል ተባለ https://telegra.ph/file…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE