“”ሜላድ የብራና ማዕድ” አውደ ርዕይ ተጠናቀቀ።
ሜላድ ጥንታዊ የብራና ጽሁፍ መጻፊያ ፣ የስዕል መሳያ እና ማሰልጠኛ ማዕከል አዘጋጅነት “ኑ ! ድንቅ ነገር እዩ !” በሚል መሪ ሀሳብ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው አውደ ርዕይ ትናንት ማምሻውን በቦሌ መድኃኒዓለም ካቴደራል በልዮ መርሐግብር ተጠናቋል።
ሜላድ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዝግጅት ማዕከል በደብረ ሊባኖሱ የሃይማኖት፣ የቅርስ፣ የታሪክ ፣ የስርዓተ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ በሆኑት በቆሞስ አባ ኪዳነ ማርያም አበበ እና በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው አማካኝነት የተቋቋመ ማዕከል ነው።
በመዝጊያው መርሐግብር ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቴሌቪዥን ዋና ሥራ አስኪያጅ ቀሲስ ዶክተር መዝገቡ ካሣ ፣ ሰባኬ ወንጌል፣ ፀሐፊና አርታኢ ዲያቆን ታደሠ ወርቁ ፣ ዕጩ ዶክተር መምህር ፋንታ ገላው ፣ ዘማሪ በርሱ ፈቃድ አንዳርጋቸው ፣ ዘማሪ ዲያቆን ፍሬዘር ደሳለኝ ፣ መምህር ወመዘምር ዳንኤል ሲሳይ ፣
ዘማሪት ፀዳለ ዳና ፣ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ፣ ምእመናን በተገኙበት በታላቅ ኪናዊ ኹነት ተጠናቋል።
“ሜላድ የብራና ማዕድ” አውደ ርዕይ እንዲሳካ ላደረጉ አካላት ምስጋና የቀረበ ሲሆን በቀጣይ ተቋሙን እየሠራ ያለውን ስራ ይበልጥ የሚያስተዋውቅ መርሐግብር እንደሚዘጋጅ በመድረኩ ተገልጿል።
ኹነቱን ያዘጋጀው መንፈሳዊ መርሐ ግብሮች በማዘጋጀት ልምድ ያለው ሎዛ ኹነቶች ነው።