አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች ፣ ክስተታዊ ጉዳዮች እና በሳምንቱ የተመረጠ እንድታዳምጡ ያዘጋጀነው አለ፡፡-ሜላት …

Reading Time: 2 minutes
አዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች ፣ ክስተታዊ ጉዳዮች እና በሳምንቱ የተመረጠ እንድታዳምጡ ያዘጋጀነው አለ፡፡

-ሜላት ቀለምወርቅ-“ዋይ” የተሰኘ ሙዚቃ በቅርቡ ይዛ ስትመጣ በግጥም እና በዜማ ወጣቱ ምረትአብ ደስታ በቅንብር ሚክስ እና ማስተሪንግ በተጨማሪም ሙዚቃውን ዳይሬክት በማድረግ ሄኖክ ድለቃ ሰርተውታል በቅርቡ ለአድማጭ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡-ሻንበል በላይነህ- ”አይዞሽ አዲስ አበባ” የቱሰኘ የሙዚቃ ስራ ሲሆን በቅርቡ አድማጮች ጆሮ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል ፡፡ በተጨማሪም ድምፃዊ ሻንበል በላይነህ ሐሙስ ምሽት በራሱ ዩትዮብ ቻናል እንደ ሚለቅ አሳውቋል፡፡-ቫኑስ ዘይዳ-”ንጉሱ ደገሰ” የተሰኘ ሙዚቃ ለ አድማጭ አደርሳለሁ ባለው መሰረት ለቆታል አድማስ ኢንተርቴመንት ገብታችሁ ተመልከቱ፡፡– ተወዳጅዋ ድምፃዊት እየሩስአሌም አስፋው ጄሪ አዲስ ነገር ይዛ እየመጣች ትገኛለች ሰሞኑን በሶሻል ሚዲያ ”tik Tok” በተባለ ማህበራዊ ሚዲያ በጎ አላማ ይዛ መታለች የድምፅ ተስዖጦ ያላቸውን ሰዎች ወደ ህዝብ ለማስተዋወቅ እየሰራች ትገኛለች፡፡ እናንተም በtik Tok ሶሻል ሚዲያ እየሩስአሌም አስፋው ብላችሁ ተስዖጦአችሁን አሳዩ ፡፡-ሮፍናን ኑሪ ጉዞውን ወደ አማሪካ ‘አትላንታ” ዲጄ ፣ የዜማ የግጥም ደራሲ ፣ የድምፅ ኦድዮ ኢንጅነር  እንዲሁም ድምፃዊ ሮፍናን ኑሪ ከምነው ሸዋ ጋር አንድ ላይ በመሆን በአሜሪካ የተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር የሙዚቃ ስራውን ሊያቀርብ ነው፡፡ሮፍናን ኑሪ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፉለት አልበሞች  የመጀመርያ አልበሙ ነፀብራቅ በኤክትሮኒስ ዳንስ ሚውዚክ በመጠቀም አድርሶን ነበር በመቀጠል  ሶስት እና ስድስት ከዛም ባለፈ የተለያዩ ሙዚቃዎችን ወደ አድማጭ አድርሷል፡፡– ፕርስቲጅ አዲስ ፤ ዛሬም እጅግ ተወዳጅ እና ወጣቱ ሙዚቀኛ የሆነውን  ወጣት ድምፃዊ ዳዊት ፅጌን  ጋብዟል:: ዳዊት የሥራ እና የህይወት ተሞክሮውን የሚያካፍልበት ሲሆን ከወዳጅ እና ድናቂዎቹ ለሚቀርቡለት ጥያቄዎችም የፊታችን ማክሰኞ ሰኔ  4 ,2016 ዓ.ም መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ይዘናል። በዕለቱ የፎቶግራፍ መነሳትና አውቶግራፍ የማስፈረም መርሃ-ግብር ይኖራል::* በዚህ ሳምንት ሙዚቃዊ ክስተት ከተነሱት ውስጥ

– የአዲስ አበባ ባህል ፣ኪነ ጥበባት ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ በደቡብ ኢትዮጲያ ክልል ከ ጋርዱላ ዞን ጋር በመተባበር የደራሼን ማህበረሰብ ቱባ የዜማ ባህል እና ፊላ የሙዚቃ ቅኝት ዙርያ ቦታው ድረስ በመገኘት ጥናት አድርገዋል፡፡ ፊላ ማለት የትንፋሽ የሙዚቃ መሳርያ ሲሆን  ፊላ ጨዋታ ለደራሼ ማህበረሰብ ዘንድ እጅግ ተወዳጅ መሆኑንም ተገልጿል፡፡– ታዋቂው አለም አቀፉ ድምፃዊ ዘ-ዊኬንድ( አቤል ተስፋዬ) ስፖቲፋይ  ባስቀመጠው የሙዚቃ ምርጫዎቹ የአንጋፋው አቀናባሪ  የኤሊያስ መልካ ቅንብር  እንደቃል ፣ ነቅቻለሁ አንዲሁም የፍቅር አዲስ “ልዑል ያስወደደኝ” ሙዚቃዎች እና ሌሎች በርካታ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎችን እንዳካተተ በዚህ ሳምንት የሰማነው ክስተት ነው፡፡– የድምፃዊ ልዑል ሲሳይ ልዑል አልበም ኮንሰርት የተደረገበት ነበር አጅበውት ኮንሰርቱን የተሳተፉት ሳሚ ዳን እና ሚካኤል በላይነህ ስራዎቻቸውን ከቶራ ባንድ ጋር አድርበዋል፡፡-በፕ/ር አሸናፊ ከበደ የተሰየመው በያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ሰኔ 1/2016 በደማቅ ሁኔታ ተመርቆ የተከፈተበት ሳምንት ነበር፡፡ ፕ/ር አሸናፊ ከበደ የያሬድ የሙዚቃ ትምህርት ቤት የመጀመርያ ዳይሬክተር የነበረ ሲሆን በህዝብ ዘንድ የሚታወቁበት አንዱ ‘እረኛው ባለ ዋሽንት” በተሰኘው ሙዚቃ ነበር፡፡* በዚህ ሳምንት የምንጋብዛችሁ የሙዚቃ አልበም ፡፡

– የድምፃዊ ሳሙኤል ተፈሪ(ሳሞን) ለውጥ የተሰኘ አልበሙ ነው በውስጡ ወደ 15 የሚጠጉ ሙዚቃዎች ሲሆሩ ወደ አንቺ ስመጣ ፣ትዝታ ፣ ቻው፣ የምኞት አባት ፣ የመጨረሻ ቀን የመሳሰሉት አሉበት፡፡ በግጥም በዜማ በራሱ ድሳሙኤል ተፈሪ (ሳሞን ) የተሰራ ሲሆንበቅንብር ቅዱስ ሐብተስላሴ ፣ ኪሩቤል ባጫ ፣ ዳግማዊ ሀብተስላሴ ፣ በድል አብ ብርሀኑ ፣ እዮብ ወርቁ ተሳትፈዋል በማስተሪንጉ ዜማስ ስቱዲዮ ሰርቶታል ፡፡Yenevibe.com ግቡና ጎብኙን እናመሰግናለን
140600cookie-checkአዳዲስ የሚወጡ ሙዚቃዎች ፣ ክስተታዊ ጉዳዮች እና በሳምንቱ የተመረጠ እንድታዳምጡ ያዘጋጀነው አለ፡፡-ሜላት …

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE