ፋና ላምሮት አስራ ሰባተኛው ምዕራፍ ሁለተኛ ምድብ አራተኛ ሳምንት ሰባት ተወዳዳሪዎችን ይዞ በዛሬ እለት ልክ…

Reading Time: 2 minutes
ፋና ላምሮት አስራ ሰባተኛው ምዕራፍ ሁለተኛ ምድብ አራተኛ ሳምንት ሰባት ተወዳዳሪዎችን ይዞ በዛሬ እለት ልክ እንደ ወትሮ ሁሉ ደምቆ አልፎአል፡፡



ምን አዲስ ነገር አለ

– በዚህኛው ምዕራፍ አዳዲስ ዳኞች ከተተኩት መሀል የሙዚቃ ባለሞያ የሹምነሽ ታዬ እና አቀናባሪ የዜማ ግጥም ደራሲ አማኑኤል ይልማ በዚህ ወር ልደታቸው ስለ ነበር ፋና ላምሮት የቀጥታ ስርጭት ሰርፕራይዝ ወይም ድንገቴ ክስተት በቦታው ተከስቶ የኬክ ቆረሳ እና ደስታውን በአደባባይ ተካፍለዋል፡፡



– ተወዳዳሪ ሱራፎል ደረጄ የታላቁን እና በብዙ ሊነገርለት የሚገባውን የድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅ ስራ ከተለያየንን በመድረክ አቅርቦ እሱም በአደባባይ ዘክሯል፡፡ ማዲንጎ ያለበትን ልብስ በመልበስ ሙዚቃውን ተጫውቷል፡፡ “አፈ ወርቅ አፈወርቅ አፈወርቅ ወልዶ ፣ አፈወርቅ አለፈ በዓለም ተወዶ” ፡፡



-በመድረኩ የተለያዩ ሙዚቃ ቀርበዋል ከቀረቡት ሙዚቃዎች ይህንን ግጥም ዜማ የሰሩ ያቀናበሩትን እናንሳ ኤልያስ መልካ ፣ ሮሀ ባንድ ፣ ኤክስፕረስ ባንድ የመሳሰሉት ፡፡ ግጥም እና ዜማ ስራ ግርማ ሐይሌ ፣ ይልማ ገብረዓብ ፣ አበበ መለሰ የመሳሰሉት ስራዎቻቸው ተደምጧል፡፡

* ዛየን ባንድ ከ ተወዳዳሪዎች ጋር ሆነው 16 ሙዚቃዎችን ተጫውተዋል …



አለማየሁ እሸቴ/ሆኛለሁ/ ፣ ዉብሸት ፍስሀ /ተለየችኝ/ ፣ ኩኩሰብስቤ/ጉብልዬ/ ፣ ንዋይ ደበበ/አዋሽም / ፣ ማዲንጎ አፈወርቅ/ ከተለያየን/ ፣ ሐመልማል አባተ/አዘንኩብህ/ ፣ ፀጋዬ እሸቱ/ሆዴ ክፉ እዳዬ/ ፣ ደረጄ ዱባለ/ፍቅሬ ታውቆ/ ፣ ጋሽ ሙሐሙድ አህመድ/ልኑርበት/ሙሉቀን መሰለ/ምስክር/ የመሳሰሉት ተሳትፈዋል፡፡

* ዳኞች ከስልትም ከስሜትም አስተያየት ሰተዋል …

ሪትም አረዳድ ፣ ፍሬዚንግ / የዜማ ሐረጋት/ ፣ ቅኝት ችግር ፣ ዜማ አረዳድ፣ ቃልን በጉልህ ማሰማት ፣ የግጥም ስህተት ፣ ሬንጅ ፣ ጉልበት አጠቃቀም ፣ ማይክራፎን አያያዝ አጠቃቀም ፣ በራል ድምፅ ማዜም ፣ ቅላፄ ፣ ድምፅ አለማልመሰል ፣ ቫይዩ አድ ፣ እጅጉን ልምምድ ማድረግ ፣ ከ ባንድ ጋር ውህደት ፣ ስሜትን መረዳት ፣ የሙዚቃ ምርጫ ፣ ተጨንቆ መዝፈን እና የመሳሰሉት ሐሳብ ተነስተዋል ፡፡

*ዳኞች ከ ሕይወታችን ስንቅ ለተወዳዳሪዎች ብርታት አስተያየት ሰተዋል ፡

-ብሩክ አሰፋ :- ቫልዩ አድ ማለት የነበረውን ሙዚቃ መሰረት አድርገን ነው የምንጨምረው፡፡



-የሹም ነሽታዬ- የድምፃዊያኖችን የተነሱበትን ሙዚቃዊ መንገድ ማወቅ ሙዚቃውን እንድንረዳው ይጠቅመናል፡፡



-አማኑኤል ይልማ- ፋና ላምሮት ብዙ ተመልካቾች አሉት እናንተ ደሞ ተመካቾችን ማሳመን አለባችሁ ፡፡



ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፉ እንጠቁም…

-አብርሀም ማርልኝ:- 59093 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት ፡፡
-ሱራፌል ደረጄ-590731 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ሄኖክ ዓለሙ-58850 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ጌታሁን ተረፈ-58842 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት ፡፡
-58553- ስንታየሁ ሀይሌ- አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡
-ቢኒያም ዘውዱ -58257 አጠቃላይ ነጥብ በማምጣት፡፡



የእለቱ ተሰናባች በፍና ላምሮት ሁለት ዙር በሁለተኛ ምድብ ቆይቷል ጥሩ ልድም ድምፅን አሳይቷል ዮሐንስ አበበ – አጠቃላይ ነጥብ ያመጣው 58237 ነው፡፡ ፋና ላምሮት አብሮነቱን ገልፆ ከ 6000 ብር ጋር አሰናብቶታል፡፡



ዘገባ ተመስገን ኡካሬ የሐጌ ልጅ
ፋና ላምሮት፡፡
ቸር ያቆየን
140310cookie-checkፋና ላምሮት አስራ ሰባተኛው ምዕራፍ ሁለተኛ ምድብ አራተኛ ሳምንት ሰባት ተወዳዳሪዎችን ይዞ በዛሬ እለት ልክ…

Share to...

Facebook
Telegram
WhatsApp
Twitter
Email
Print
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡
ልጅ ተሙኤል

ልጅ ተሙኤል

ጋዜጠኛ እና የሙዚቃ ባለሞያ ተመስገን ኡካሬ እባላለሁ ኢካሽ የጋዜጠኝነት ማሰልጠኛ ማዕከል ተምሬ ተመርቄአለሁ ፡፡ እናም አሁን በአራዳ fm 95.1ላይ የኔቫይብ አባል የሙዚቃ አዘጋጅ ነኝ የኔ ጊዜ የሚል ፕሮግማም ፡፡ በሙዚቃ ውስጥ ዜማ ግጥም ፅፋለሁ የሙዚቃ መሳርያም እጫወታለሁ አሁን ላይ ሲደርታ የሙዚቃ ትምህርት ቤት ተማሪ ነኝ ፡፡

Any Thought?

Be part of the Community! Comment, connect, spread some joy and let the fun begin!

YOU MAY ALSO LIKE