ጋዜጠኛ መሠለ ገ/ህይወት ከዜናው ዓለም ወደ መዝናኛው ዓለም ሊሸጋገር ነው።
በዜና አንባቢነት የሚታወቀው አንጋፋው ጋዜጠኛ መሠለ ገ/ህይወት በመዝናኛው ዘርፍ ሊመጣ ነው።
ላለፉት 18 ዓመታት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በዜና አንባቢነት ሲያገለግል የቆየው መሠለ በቅርቡ “መሴ ሾዉ” የተሠኘ የምሽት መዝናኛ ፕሮግራም በአባይ ቲቪ እንደሚጀምር ታውቋል።
መሴ ሾዉ የተሠኘው የምሽት የመዝናኛ ፕሮግራም (late night show) የሠርጌለታ፣ የሙዚቀኞች ብፌ፣ የእንግዳ ቆይታ እንዲሁም እግሬ ሲደርስ የተሰኙ አዝናኝ መሠናዶዎች የተካተቱበት ነው።
ፕሮግራሙ በየሣምንቱ ቅዳሜ ምሽት በአባይ ቲቪ ከመተላለፉ ባሻገር መሴ ሾው በሚል ስያሜ በተከፈተ በራሱ የዩቲዩብ ቻናል ለተመልካች የሚደርስ ይሆናል።
ጋዜጠኛ መሠለ ከሁለት ዓመታት በፊት የመልካሙ ተበጀንና የንዋይ ደበበን ዘፈኖች በመጫወት የመዝናኛ ተሥጥዖውን ማሣየቱና ተመልካቾችን ማሥደመሙ ይታወሳል።
መረጃው የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ነው።
Via: Event Addis